ኢቢኤስ አዲስ ነገር ዲጂታል ሚዲያ የሚያዚያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም የምሽት የሀገር ውስጥ ዋና ዋና ዜናዎች፦
✅በሳዑዲአረቢያ በወንጀል ተጠርጥረው ሞት የተፈረደባቸው ዜጎች የፍርድ ውሳኔ እንዲለዝብ ለማድረግ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
✅ቻይና ኢትዮጵያን ጨምሮ ለ53 የአፍሪካ ሀገራት ከነገ ጀምሮ በሁሉም የምርት አይነቶች ላይ የዜሮ ታሪፍ ፖሊሲን ተግባራዊ እንደምታደርግ አስታወቀች፡፡
✅ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት አር ኤስ ኤፍ ባወጣው የፕሬስ ነጻነት ሁኔታ በሚመዘንበት የ2026 ዓለም አቀፍ ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያ ከ180 ሀገራት 148ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ገለጸ፡፡
✅የፍትህ ሚኒስቴር መነሻቸውን ከአማራና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች በማድረግ ዋና መዳረሻቸውን አዲስ አበባ ባደረጉ የሕፃናት ዝውውር ላይ የሚስተዋለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰትና በሰው የመነገድ ወንጀልን ለመግታት፣ የተቀናጀ የጋራ አሠራር መዘርጋት የግድ እንደሚል ገልጿል፡፡
✅በተያዘው የ2018 ግማሽ አመት ከውጭ ንግድ ታክስ ለመሰብሰብ ከታቀደው ገቢ 51 በመቶ ብቻ መሰብሰቡን የገንዘብ ሚኒስቴር ገለፀ፡፡
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
@ebstvnews
www.ebstv.tv
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram