avatar
Cooperative Bank of Oromia
21.03.2026 17:31
የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ የዓለም ዋንጫ መመልከት የሚያስችል የሎተሪ ዕጣ ይፋ አደረገ

መጋቢት 12፣ 2018 (አራዳ ኤፍ ኤም) የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ከVISA ጋር በመሆን በሰሜን አሜሪካ በሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ላይ በተመልካችነት ለመሳተፍ የሚያስችል ዕጣ የሚያስገኘውን "ጉዞ ወደ ፊፋ የዓለም ዋንጫ 2026" ዘመቻ በይፋ አስጀምሯል።

ዕጣው በካርዱ ግብይት ለሚፈጽሙ የኮፕ VISA ካርድ ደንበኞች የዕጩነት የዕጣ ቁጥር በማደል ዕድለኛ ለሚሆኑ ሁለት፥ ደንበኞች እያንዳንዳቸው በአንድ ተጨማሪ ሰው ታጅበው ቪዛ፣ የደርሶ መልስ የአየር ትኬት፣ ሆቴልና ምግብ፣ የጨዋታ ትኬቶችና ተዛማጅ ወጪዎችን ያካተተ ሙሉ ፓኬጅ ያስገኛል ተብሏል።

በዕጣው ብቁ የሚያደርጉ ግብይቶችም፥ በቪዛ ክላሲክ ዴቢት ካርዶች የተከናወኑ የሀገር ውስጥ ፖስ እና የኢ-ኮሜርስ ክፍያዎች(በመደበኛና በኮፕባንክ አልሁዳ) የሚከናወኑ ግብይቶች፣ በቪዛ ክላሲክ ፕሪ ፔይድ ካርዶች የሚፈጸሙ ዓለም አቀፍና ኦንላይን ክፍያዎች፣ በቪዛ ፕላቲኒየም ፕሪ ፔይድ ካርዶች የሚከናወኑ ፕሪሚየም ዓለም አቀፍ ግብይቶችና በሁሉም ምድቦች የሚከናወኑ ‘ኮንታክትለስ’ ክፍያዎች መሆናቸውንም አስታውቋል።



ተጨማሪ ለማንበብ https://web.facebook*.com/share/p/1FQzTETNvE/


የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ

Youtube:https://www.youtube.com/@aradafm95.1

Tiktok:https://www.tiktok.com/@aradafm95.1offical

Telegram:-@Arada_Fm

Telegram:-@aradaFmdigital

Facebook*:-https://web.facebook*.com/aradafm

@Arada_Fm
10
👍 2
1 2 8.4K
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Cooperative Bank of Oromia

79K
Coopbank, a fast-growing bank in Ethiopia, is passionately committed to empowering communities and transforming lives. Rooted in our community, we deliver innovative services that meet customer needs helping you bank smarter and live better.
Открыть в Telegram