avatar
Commercial Bank of Ethiopia - Official
@combankethofficial
07.04.2026 22:17
የጥንቃቄ መልዕክት ከባንካችሁ!
ክቡራን ደንበኞቻችን ፤
********************
በአሁኑ የዲጂታል ዘመን ስልክዎ የባንክ ሂሳብዎ መሆኑን ያውቃሉ? በጥቃቅን ስህተቶች ለዘመናት የቆጠቡትን ጥሪት ለነጣቂዎች አሳልፈው እንዳይሰጡ የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች ያድርጉ፦
1) ሚስጥራዊነትን ይጠብቁ፦ የባንክ ሂሳብ ቁጥርዎን፣ የሞባይል ባንኪንግ የይለፍ ቃል (Password/PIN) እና በስልክዎ የሚላኩ የማረጋገጫ ቁጥሮችን (OTP) ለማንም አሳልፈው አይስጡ።
2) ከአጠራጣሪ ጥሪዎችና ሊንኮች ይጠንቀቁ፦ ባንኩ በስልክ ደውሎ ሚስጥራዊ ቁጥርዎን አይጠይቅም። ማንኛውንም አጠራጣሪ ሊንክ አይክፈቱ፤ የማያውቁትን ስልክ አይመልሱ።
3) ስልክዎ ሲጠፋ፦ ስልክዎ ቢጠፋ ወይም ቢሰረቅ በአፋጣኝ በ951 በመደወል ወይም በአቅራቢያዎ በሚገኝ ቅርንጫፍ በመቅረብ የባንክ አገልግሎትዎ እንዲታገድ ያድርጉ።
4) ጠንካራ የይለፍ ቃል ይጠቀሙ፦ የሞባይል ባንኪንግ የይለፍ ቃልዎን በቀላሉ የማይገመት (ቢያንስ 6 ዲጂት) ያድርጉ። ከባንክ የተላከልዎትን ጊዜያዊ ቁጥር ወዲያውኑ ይቀይሩ፤ ከስልክዎም ላይ ያጥፉት።
5) ስልክዎን ለሰው አይስጡ፦ ስልክዎን ለጥገና ወይም ለሌላ ጉዳይ ለሰው ሰጥተው ሲቀበሉ አጠራጣሪ መተግበሪያዎች (Apps) አለመጫናቸውን ያረጋግጡ።
6) የማህበራዊ ሚዲያ ደህንነት፦ በስራ ማስታወቂያ ወይም በሽልማት ስም የሚላኩ የባንክ ወይም የቴሌግራም/ዋትስአፕ ማረጋገጫ ቁጥሮችን ለሌላ አካል በመስጠት የባንክ ሒሳብዎ ተጠልፎ ለወንጀል እንዳይውል ይጠንቀቁ።
ሁልጊዜም ንቁ እና ጠንቃቃ በመሆን ገንዘብዎን ይጠብቁ!
#የኢትዮጵያ_ንግድ_ባንክ #cbe #FraudAlert
35
👍 10
11 7 4.8K
avatar
Commercial Bank of Ethiopia - Official
@combankethofficial
07.04.2026 21:57
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ዜጎች በሀገሪቱ የልማት ስራዎች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠረ እንደሚገኝ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኦሮሚያ ዲያስፖራ ማህበር ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ።
**************************
በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቢዝነስ ኤክስኪዩቲቭ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ደረጄ ፉፋ እንደገለጹት፤ ስምምነቱ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሀገራዊ ልማት ላይ ያላቸውን ሚና ለማጎልበት ትልቅ ፋይዳ አለው።

ስምምነቱ ዲያስፖራው በሀገር ውስጥ ኢንቨስትመንት ላይ በስፋት እንዲሰማራ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ ያብራሩት አቶ ደረጄ ባንካችን ለዲያስፖራው ማህበረሰብ የሚመጥኑ የቁጠባ፣ የብድርና የገንዘብ መላኪያ አማራጮችን በስፋት ማመቻቸቱንም አክለዋል።

የባንካችን የሪቴይል ባንኪንግ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ደሳለኝ አለሙ በበኩላቸው፤ ማህበሩ ባንካችን የሚያቀርባቸውን አገልግሎቶች ለዲያስፖራው ተደራሽ ለማድረግ እንደ ድልድይ ሆኖ እንደሚያገለግል ገልጸዋል።
ዲያስፖራው የመኪናና የቤት ግዢ ብቻ ሳይሆን፣ ከአነስተኛ እስከ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ላይ እንዲሰማራ የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች መመቻቸታቸውንም አስረድተዋል።

የኦሮሚያ ዲያስፖራ ማህበር ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ሳራ ሀሰን በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለዲያስፖራው ልዩ ቅርንጫፎችን ከመክፈት ጀምሮ እንደ ኢትዮ ዳይሬክት (EthioDirect) እና ሲቢኢ ኮኔክት (CBEConect) ያሉ ዘመናዊ የገንዘብ መላኪያ መተግበሪያዎችን ማቅረቡ በትብብር ለመስራት እንደሚያስችላቸው ገልጸዋል።

ባንኩ የሀገር አለኝታ መሆኑን የጠቀሱት ፕሬዝዳንቷ፤ ዲያስፖራው የአገልግሎቶቹ ተጠቃሚ በመሆን በሀገሩ ልማት ላይ አሻራውን እንዲያኖር ጥሪ አቅርበዋል።
#የኢትዮጵያ_ንግድ_ባንክ #cbe #diaspora #oromia_diaspora
11
👏 2
4.5K
avatar
Commercial Bank of Ethiopia - Official
@combankethofficial
07.04.2026 17:53
ሁሉንም ባሉበት
በሲቢኢ ዲጂታል የባንክ አገልግሎት
ገንዘብዎን እና ጊዜዎን ይቆጥቡ!
************

�� ገንዘብ ለመላክ እና የተለያዩ ክፍያዎችን ለመፈፀም
�� የተለያዩ የባንክ አገልግሎቶችን ለማግኘት
�� ግብር እና ለተለያዩ መንግስታዊ አገልግሎቶች ክፍያ ለመፈፀም
�� የመብራት እና ውሀ ክፍያ ለመፈፀም
�� የጉዞ ትኬት ክፍያ ለመፈፀም
�� የአየር ሰዓት ለመሙላት
�� .....................

የትም መሄድ ሳይጠበቅብዎት ካሉበት ሆነው ከጥሬ ገንዘብ ነፃ
በሲቢኢ ዲጂታል የባንክ አገልግሎት አማራጮች ይጠቀሙ!
**********
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
#cbe #digitalbanking #cashless
21
👍 4
13 1 8.7K

Commercial Bank of Ethiopia - Official

198.1K
Commercial Bank of Ethiopia is the leading bank in Ethiopia, established in 1942. Pioneer to introduce modern banking to the country with 1,971 branches and service outlet across the country.
@ www.facebook*.com/combanketh
@ www.twitter.com/combankethiopia
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram