avatar
Commercial Bank of Ethiopia - Official
@combankethofficial
07.04.2026 21:57
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ዜጎች በሀገሪቱ የልማት ስራዎች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠረ እንደሚገኝ ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኦሮሚያ ዲያስፖራ ማህበር ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ።
**************************
በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቢዝነስ ኤክስኪዩቲቭ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ደረጄ ፉፋ እንደገለጹት፤ ስምምነቱ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሀገራዊ ልማት ላይ ያላቸውን ሚና ለማጎልበት ትልቅ ፋይዳ አለው።

ስምምነቱ ዲያስፖራው በሀገር ውስጥ ኢንቨስትመንት ላይ በስፋት እንዲሰማራ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ ያብራሩት አቶ ደረጄ ባንካችን ለዲያስፖራው ማህበረሰብ የሚመጥኑ የቁጠባ፣ የብድርና የገንዘብ መላኪያ አማራጮችን በስፋት ማመቻቸቱንም አክለዋል።

የባንካችን የሪቴይል ባንኪንግ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ደሳለኝ አለሙ በበኩላቸው፤ ማህበሩ ባንካችን የሚያቀርባቸውን አገልግሎቶች ለዲያስፖራው ተደራሽ ለማድረግ እንደ ድልድይ ሆኖ እንደሚያገለግል ገልጸዋል።
ዲያስፖራው የመኪናና የቤት ግዢ ብቻ ሳይሆን፣ ከአነስተኛ እስከ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ላይ እንዲሰማራ የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎች መመቻቸታቸውንም አስረድተዋል።

የኦሮሚያ ዲያስፖራ ማህበር ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ሳራ ሀሰን በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለዲያስፖራው ልዩ ቅርንጫፎችን ከመክፈት ጀምሮ እንደ ኢትዮ ዳይሬክት (EthioDirect) እና ሲቢኢ ኮኔክት (CBEConect) ያሉ ዘመናዊ የገንዘብ መላኪያ መተግበሪያዎችን ማቅረቡ በትብብር ለመስራት እንደሚያስችላቸው ገልጸዋል።

ባንኩ የሀገር አለኝታ መሆኑን የጠቀሱት ፕሬዝዳንቷ፤ ዲያስፖራው የአገልግሎቶቹ ተጠቃሚ በመሆን በሀገሩ ልማት ላይ አሻራውን እንዲያኖር ጥሪ አቅርበዋል።
#የኢትዮጵያ_ንግድ_ባንክ #cbe #diaspora #oromia_diaspora
11
👏 2
4.5K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Commercial Bank of Ethiopia - Official

198.1K
Commercial Bank of Ethiopia is the leading bank in Ethiopia, established in 1942. Pioneer to introduce modern banking to the country with 1,971 branches and service outlet across the country.
@ www.facebook*.com/combanketh
@ www.twitter.com/combankethiopia
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram