avatar
Commercial Bank of Ethiopia - Official
@combankethofficial
08.04.2026 10:01
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳር ፋይናንስ ቢሮ በኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎት አብረው ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡
• ስምምነቱ የቢሮውን የፋይናንስ ቁጥጥርና አሰራር ዘመናዊ ለማድረግ ይረዳል ተብሏል፡፡
*****************


በስምምነቱ ወቅት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሆል ሴል ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር እስክንድር አስፋው በሰጡት መግለጫ ባንካችን የዲጅታል ኢትዮጵያ ግብን እውን ለማድረግ ከተለያዩ ተቋማት ጋር እየሰራ እንደሚገኝና ይህ ስምምነት የዚሁ አካል መሆኑን ገልፀዋል፡፡

99 በመቶ የሚሆኑት የፌደራል ተቋማት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረው፣ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የፋይናንስ ቢሮም የዚሁ አገልግሎት ተጠቃሚ በመሆኑ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ዘመናዊና ቀልጣፋ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡

መስተዳደሩ በ119 ወረዳዎች፤ 600 ትምህርት ቤቶችና ጤና ጣቢያዎች ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለውን ሂሳብ በተማከለ መልኩ በኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎት ለማንቀሳቀስ ስምምነቱ እንደሚያስችል ዶ/ር እስክንድር አመልክተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ምክትል ከንቲባ ማዕረግ የፋይናነስ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን በበኩላቸው እንደተናገሩት በከተማው የሚካሄዱ በርካታ የልማት ስራዎችን የፋይናንስ እንቅስቃሴን 24 ሰዓት ለመቆጣጥርና ለማስተዳዳር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢንተርኔት ባንኪንግ አገልግሎት ትልቅ ሚና አለው፡፡

ስምምነቱ ግልጸኝነትን፤ ተጠያቂነትንና ቀልጣፋ አሰራርን ስለሚያሰፍን የመስተዳድሩን የፋይናንስ ግቦች ለማሳካት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ተመራጭ ማድረጋችን ትክክለጫ አካሄድ ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በውሃና የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያ፣ በትራፊክ ቅጣት ክፍያዎች፣ በቤት ልማት እና በሌሎች ዘርፎችም ከመስተዳድሩ ጋር በዲጅታል ባንኪንግ በኩል አብሮ እየሰራ ነውም ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ በዲጅታል ባንኪንግ አማራጮች በከ15.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ገንዘብ መዘዋወሩ ታውቋል፡፡
17
👍 5
👏 1
1 6 17.5K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Commercial Bank of Ethiopia - Official

198.1K
Commercial Bank of Ethiopia is the leading bank in Ethiopia, established in 1942. Pioneer to introduce modern banking to the country with 1,971 branches and service outlet across the country.
@ www.facebook*.com/combanketh
@ www.twitter.com/combankethiopia
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram