avatar
Commercial Bank of Ethiopia - Official
@combankethofficial
07.04.2026 16:03
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መቐለ ዲስትሪክት 'ተግተን እናገለግላለን፣ በፍቅር እናጋራለን' በሚል መሪ ቃል የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የማዕድ ማጋራት መርሀ ግብር አከናውኗል።
• ዲስትሪክቱ 1.6 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ ነው ለ204 ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች መዓድ ያጋራው።
**************
በመርሃግብሩ ላይ የተገኙት የመቐለ ዞን ሃገረ ስብከት ተወካይ ቆሞስ አባ ወ/ብርሃን ወ/ሳሙኤል ባንኩ ላከናወነው የተቀደሰ ተግባር አመስግነው፣ ሕብረተሰቡም የባንኩን አርአያነት በመከተል ያለው ለሌለው በማካፈል በዓሉን በመረዳዳትና በመተሳሰብ እንዲያሳልፍ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመቐለ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ ልሳነ ወርቅ ባንካችን ላለፉት 84 ዓመታት ከዕለት ተዕለት የባንክ አገልግሎት ባሻገር ለታላላቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች በሚሰጠው የፋይናንስ አገልግሎት የሃገር አለኝታ መሆን መቻሉን ተናግረዋል።

ባንኩ ከዚህ በተጨማሪ በማኅበራዊ ሃላፊነት ስራዎቹም የሕብረተሰቡን ችግር ለመቅረፍ በዓይነትና በገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ለብዙዎች እየደረሰ እንደመጣ የገለፁት አቶ ኤልያስ፣ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የትንሳኤ በዓልን በማስመልከት 1.6 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ ለ204 ወገኖች መዓድ በማጋራት አለኝታነቱን ማሳየቱን ተናግረዋል።

የመቐለ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ተወካይ አቶ ዘመንፈስቅዱስ ፍስሃ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመቐለ ከተማ በርካታ የልማት ስራዎች ላይ አስተዋፅኦ ከማበርከቱ በተጨማሪ በበዓላት ወቅት ድጋፍ ለሚሹ የሕብረተሰብ ክፍሎች ለሚያደርገው እገዛ በከተማ አስተዳደሩ ስም ከልብ አመስግነዋል። ሌሎች ተቋማትም የባንኩን አራያነት እንዲከተሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ድጋፍ የተደረገላቸው ነዋሪዎች በበኩላቸው ባንኩ የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ ያበረከተው የምግብ ፍጆታና የገንዘብ ድጋፍ ወቅቱን ያገናዘበ መሆኑን ጠቁመው፣ ይህም ባንኩ ለማህበረሰቡ ያለውን ቅርበት እና አጋርነት እንደሚያመላክት ተናግረዋል።

ባንካችን የዘንድሮውን የትንሣኤ በዓል በማስመልከት በሁሉም ዲስትሪክቶች ስር በሚገኙ ጸ/ቤቶቸ አማካኝነት ከአስራ አንድ ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወገኖች የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር እያከናወነ ይገኛል፡፡
12
👏 3
2 2 8.9K

Обсуждение 2

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Commercial Bank of Ethiopia - Official

198.1K
Commercial Bank of Ethiopia is the leading bank in Ethiopia, established in 1942. Pioneer to introduce modern banking to the country with 1,971 branches and service outlet across the country.
@ www.facebook*.com/combanketh
@ www.twitter.com/combankethiopia
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram