avatar
Commercial Bank of Ethiopia - Official
@combankethofficial
06.04.2026 15:33
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጎንደር ዲስትሪክት የ2018 ዓ.ም የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረገ ለአቅመ ደካሞቸ ማዕድ አጋራ።
**********

“ተግተን እናገለግላለን፤ በፍቅር እናጋራለን” በሚል መሪ ቃል በጎንደር ዲስትሪክት በተዘጋጀው በዚህ መርሐ ግብር ላይ የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኜ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የማእከላዊ ጎንደር አገረ ስብከት ጽ/ቤት ሥራ አሥኪያጅ ሊቀ ሥልጣናት ቆሞስ አባ ዮሴፍ ደስታ፤ የጎንደር ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ መሉጌታ የኔአለም እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ ከ200 በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች በነፍስ ወከፍ 25 ኪሎ የዳቦ ዱቄት፣ 5ሊትር የምግብ ዘይት፣ ለበአል መዋያ የሚሆን 1,500 ብር ከክብር እንግዶቹ እጅ የተቀበሉ ሲሆን ለተደረገላቸው ስጦታም ባንኩን አመስግነዋል። ይህን የቆየ የመረዳዳት ባህላችንን አጠንከሮ መያዝ እንደሚገባ እና የባንኩ ተግባርም ለሌሎች ተቋማት አርአያ እንደሆነም ገልጸዋለ።

ባንካችን የዘንድሮውን የትንሣኤ በዓል በማስመልከት በሁሉም ዲስትሪክቶች ስር በሚገኙ ጸ/ቤቶቸ አማካኝነት ከአስራ አንድ ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወገኖች የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር እያከናወነ ይገኛል፡፡
25
👏 5
🔥 4
3 5 10.9K

Обсуждение 3

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Commercial Bank of Ethiopia - Official

198.1K
Commercial Bank of Ethiopia is the leading bank in Ethiopia, established in 1942. Pioneer to introduce modern banking to the country with 1,971 branches and service outlet across the country.
@ www.facebook*.com/combanketh
@ www.twitter.com/combankethiopia
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram