avatar
Commercial Bank of Ethiopia - Official
@combankethofficial
06.04.2026 14:51
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የማስተርካርድን (Mastercard) በመጠቀም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ላስመዘገበው አፈጻጸም ከማስተርካርድ ዕውቅና አገኘ።
*******************
ዛሬ መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም በማስተርካርድ የምስራቅ አፍሪካ ካንትሪ ማኔጀር እና ሲኒየር ምክትል ፕሬዚዳንት ሚስተር ሼርያር አሊ የሚመራው የልዑካን ቡድን በባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት በመገኘት፣ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ዕውቅናውን አበርክተዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለዚህ ዕውቅና የበቃው ባለፉት ስድስት ወራት የማስተርካርድን ጌትዌይ (MPGS) አገልግሎትን በመጠቀም በየወሩ በአማካይ ከ4 ሚሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ወደ ሀገር ቤት እንዲገባ በማስቻሉ መሆኑ ተገልጿል።

የልዑካን ቡድኑ ከባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች እና የወደፊት አቅጣጫዎች ላይ ጥልቅ ውይይት ያደረገ ሲሆን፣ ባንኩ ከማስተርካርድ ጋር እያከናወነ ስላለው አገልግሎትና ስለደንበኞች እርካታ ሰፊ ምክክር አድርገዋል።

በውይይቱ ላይ የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ እንደተናገሩት፣ የዲጂታል ባንክ አገልግሎት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደረ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ደንበኞች ዓለም አቀፍ አገልግሎቶችን በቀላሉ የሚያገኙበትና ግብይቶችን የሚያቀላጥፉበት የፈጠራ ሥራዎች ሊጠናከሩ ይገባል ብለዋል።

አቶ አቤ ማስተርካርድም በተመሳሳይ የደንበኞችን ፍላጎት ለማርካትና ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ ሊሠራ እንደሚገባው አመልክተዋል።

በማስተርካርድ የምስራቅ አፍሪካ ካንትሪ ማኔጀር እና ሲኒየር ምክትል ፕሬዚዳንት ሚስተር ሼርያር አሊ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ90 በመቶ በላይ የዲጂታል ባንክ አገልግሎት የሚሰጥ ግዙፍ ተቋም መሆኑን ጠቅሰው፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ በማስተርካርድ በኩል ያስመዘገበው ውጤት ሊያስመሰግነው እንደሚገባ ገልጸዋል።

በቀጣይም በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለውን አጋርነት በማጠናከር የአገልግሎት ጥራትንና የደንበኞችን እርካታ ለማሳደግ ተከታታይ ውይይቶች እንደሚደረጉ ታውቋል።
12
👍 5
3 4 10.8K

Обсуждение 3

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Commercial Bank of Ethiopia - Official

198.1K
Commercial Bank of Ethiopia is the leading bank in Ethiopia, established in 1942. Pioneer to introduce modern banking to the country with 1,971 branches and service outlet across the country.
@ www.facebook*.com/combanketh
@ www.twitter.com/combankethiopia
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram