avatar
Commercial Bank of Ethiopia - Official
@combankethofficial
04.04.2026 20:31
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመተሳሰብ እሴት ተምሳሌት መሆኑ ተገለፀ።
ባንካችን በባህርዳር ዲስትሪክት ለ244 ድጋፍ የሚሹ ነዋሪዎች ማዕድ አጋርቷል።
*************
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባህር ዳር ዲስትሪክት "ተግተን እናገለግላለን፣ በፍቅር እናጋራለን" በሚል መሪ ቃል የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የማዕድ ማጋራት መርሀ ግብር አከናውኗል።
በስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የባህርዳር እና የሰሜን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሀም እንዳሉት ለሀገር አለኝታና አጋር የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማዕድ ማጋራቱ የመተሳሰብ እና ችግረኞችን የመርዳት እሴት አርዓያነቱን ያሳያል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰሜን ቀጠና ም/ፕሬዚዳንት አቶ ሳሙኤል ተስፋሁነኝ ባንካችን ከዕለት ተዕለት የባንክ አገልግሎት እና ለሀገር ልማት ከሚሰጠው የፋይናንስ አገልግሎት በተጨማሪ በማህበራዊ ሃላፊነት ስራዎቹ በዓይነትና በገንዘብ ድጋፍ ለብዙዎች እየደረሰ መሆኑን ተናግረዋል።
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ አስራቴ ሙጬ ባንኩ በበርካታ የከተማዋ የልማት ስራዎች አስተዋፅኦ ከማበርከት በተጨማሪ በበዓላት ወቅት ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚያደርገው ድጋፍ በአርዓያነት የሚያስመሰግነው ነው ብለዋል።
የባህር ዳር ከተማ አስተዳዳር የሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ሃላፊ ወ/ሮ ሰብለ ዘውዱ ባንካችን ለችግረኞች ለበዓል ድጋፍ በማድረጉ አመስግነዋል። የከተማዋን ሴቶች ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ባንኩ ለሚያደርገው ድጋፍም አመስግነዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የባህርዳር ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ደመወዝ ባልቢ በማዕድ ማጋራቱ 1.6 ሚሊዮን ብር በሆነ ወጪ በከተማ አስተዳደሩ ለተለዩ 244 ድጋፍ የሚሹ ወገኖች 25ኪ ዱቄት፣ 5 ሊትር የምግብ ዘይት እና የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ መደረጉን ገልፀዋል።
20
👍 6
4 1 12.8K

Обсуждение 4

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Commercial Bank of Ethiopia - Official

198.1K
Commercial Bank of Ethiopia is the leading bank in Ethiopia, established in 1942. Pioneer to introduce modern banking to the country with 1,971 branches and service outlet across the country.
@ www.facebook*.com/combanketh
@ www.twitter.com/combankethiopia
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram