avatar
Commercial Bank of Ethiopia - Official
@combankethofficial
04.04.2026 20:06
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ልዑክ እየተገነባ ያለውን የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ጎበኘ።
********************
​በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የማዕከላዊ ሪጅን ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሙሉነህ ለማ የተመራ ልዑክ በቢሾፍቱ እየተገነባ ያለውን ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ጎብኝቷል።

​በጉብኝቱ ወቅት አቶ ሙሉነህ ለማ እንደገለጹት፤ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ሀገሪቱን እጅግ ከፍ እያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ለዚህም የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ፣ የታላቁ የህዳሴ ግድብ እና የኮሪደር ልማት ስራዎች እንደ ምሳሌ የሚጠቀሱ መሆናቸውን ተናግረዋል።

​በአቶ ሙሉነህ የተመራው ልዑክ ከአውሮፕላን ማረፊያው ግንባታ ጋር ተያይዞ ከቀያቸው ለተነሱ አርሶ አደሮች የተገነቡ የመኖሪያ ቤቶችን እና የአግሮ ፕሮሰሲንግ ማዕከልን በተጨማሪ ጎብኝቷል።

​የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቀያቸው ለተነሱ አርሶ አደሮች የሰራው ስራ አርአያነት ያለው ተግባር መሆኑን አቶ ሙሉነህ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የእነዚህን አርሶ አደሮች የህብረት ስራ ማህበር በፋይናንስ እና በሙያ ረገድ እንደሚደግፍም አቶ ሙሉነህ  አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ምሰሶ በመሆን ታሪክ እየሰሩ ያሉ ተቋማት መሆናቸውንም ነው አቶ ሙሉነህ  የተናገሩት።
10
👍 9
👏 2
😁 2
3 11.9K

Обсуждение 3

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Commercial Bank of Ethiopia - Official

198.1K
Commercial Bank of Ethiopia is the leading bank in Ethiopia, established in 1942. Pioneer to introduce modern banking to the country with 1,971 branches and service outlet across the country.
@ www.facebook*.com/combanketh
@ www.twitter.com/combankethiopia
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram