avatar
Commercial Bank of Ethiopia - Official
@combankethofficial
03.04.2026 15:20
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የትንሳዔ በዓልን ምክንያት በማድረግ በወሊሶ ከተማ ከ200 በላይ ለሚሆኑ ወገኖች ማዕድ አጋራ።
*************
መርሐ-ግብሩ “ተግተን እናገለግላለን፤ በፍቅር እናጋራለን!” በሚል መሪ ቃል የተከናወነ ሲሆን በከተማው አስተዳደር ለተለዩ ለ200 ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች 25 ኪሎ ስንዴ ዱቄት፣ አምስት ሊትር ፈሳሽ ዘይት እና የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምዕራብ ሪጅን ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ መልካሙ ዴሲሳ ባንኩ ከ90 ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ የትንሳኤ በዓልን ምክያት በማድረግ ማዕድ በማጋራት ለሕብረተሰባችን ያለዉን አለኝታነት እያሳየ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የወሊሶ ከተማ ከንቲባ አቶ ገመቹ አረዳ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በሚገባ እየተወጣ ያለ ባንክ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በተጨማሪም ባንኩ በወሊሶ ከተማ እድገት ላይም የራሱን አሻራ እያኖረ ያለ ባንክ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ድጋፍ የተደረገላቸዉ ወገኖች በበኩላቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን አመስግነዋል፡፡

በፕሮግራሙ ማጠቃለያ ላይ በወሊሶ ከተማ በመገንባት ላይ የሚገኘዉን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የገበያ ማዕከል ህንፃ ተጎብኝቷል፡፡
👍 18
11
👏 6
3 3 14.2K

Обсуждение 3

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Commercial Bank of Ethiopia - Official

198.1K
Commercial Bank of Ethiopia is the leading bank in Ethiopia, established in 1942. Pioneer to introduce modern banking to the country with 1,971 branches and service outlet across the country.
@ www.facebook*.com/combanketh
@ www.twitter.com/combankethiopia
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram