avatar
Commercial Bank of Ethiopia - Official
@combankethofficial
03.04.2026 13:24
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 5ኛውን የሕግ ተገዥነት ቀን (Compliance Day) እያከበረ ነው::
****************
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ "የፋይናንስ ወንጀሎችን በግልጽነት በመዋጋት የባንካችንን እምነትና ታማኝነት መገንባት" በሚል መሪ ቃል፣ 5ኛውን የሕግ ተገዥነት (Compliance Day) በዛሬው ዕለት በዋና መስሪያ ቤቱ በድምቀት ማክበር ጀምሯል።

ባንኩ ላለፉት አራት ተከታታይ ዓመታት ሲያደርገው እንደቆየው ሁሉ፣ ዘንድሮም ለአምስተኛ ጊዜ የሚከበረው ይህ ዕለት በዋናነት በፋይናንስ ዘርፉ ላይ የሚስተዋሉ ሕገ-ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከልና የደንበኞችን እምነት ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

የዕለቱን መርሐ-ግብር በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ፣ ባንኩ ለሕግ ተገዥነት የሚሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት ገልጸው ለታዳሚዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመርሐ-ግብሩ ላይ የፍትህ ሚኒስቴር ድኤታ አቶ ቸርነት ወርዶፋ እና የኢትዮጵያ የፋይናንስ ደህንነት ተቋም ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ ተገኘተዋል።የኢትዮጵያ የፋይናንስ ደህንነት ተቋም ዋና ዳይሬክተር እንዳሉት የፋይናንስ ተቋማት የሕግ ተገዥነትን ማረጋገጥ ለሀገር ኢኮኖሚ ደህንነት ያለውን ፋይዳ አጽንኦት ሰጥተውበታል።

በቆይታውም ከተለያዩ ተቋማት በመጡ ምሁራን አማካኝነት በዘርፉ ዙሪያ ሰፊ የፓናል ውይይት እንደሚካሄድ የታወቀ ሲሆን፣የባንኩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የባንኩ ሠራተኞች፣ከተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት የተጋበዙ ተወካዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው ምሁራን በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
17
👍 10
7 13K

Обсуждение 7

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Commercial Bank of Ethiopia - Official

198.1K
Commercial Bank of Ethiopia is the leading bank in Ethiopia, established in 1942. Pioneer to introduce modern banking to the country with 1,971 branches and service outlet across the country.
@ www.facebook*.com/combanketh
@ www.twitter.com/combankethiopia
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram