avatar
Commercial Bank of Ethiopia - Official
@combankethofficial
02.04.2026 17:43
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ቪዛ እድለኛ ደንበኞች የ2026™ የፊፋ ዓለም ዋንጫን በአካል መታደም የሚችሉበትን ሽልማት ይፋ አደረጉ።
*************


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ቪዛ በጋራ በመሆን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ቪዛ ካርድ ተጠቅመው ክፍያ ለሚፈጽሙ ደንበኞች በዩናይትድ ስቴትስ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ አዘጋጅነት በሚካሄደው የ2026™ የፊፋ ዓለም ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎችን ሙሉ ወጫቸው ተሸፍኖ መታደም የሚያስችላቸውን ጉዞ እና የተለያዩ ተጨማሪ ሽልማቶችን ማግኘት የሚችሉበትን እድል ይፋ አድርገዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲጂታል ባንኪንግ ምክትል ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ሚደቅሳ ቶሎሳ ባንኩ በተለያየ ጊዜ አገልግሎቶቹን ለሚጠቀሙ ደንበኞቹ ሽልማት እንደሚሰጥ አስታውሰው፣ አሁንም ከቪዛ ጋር በመተባበር ደንበኞችን የፊፋ ዓለም ዋንጫን በአካል መታደም የሚያስችል እድል ማመቻቸቱን ገልፀዋል።

አቶ ሚደቅሳ ባንኩ ከቪዛ ጋር በርካታ ስራዎችን እንደሚሰራ ገልፀው፣ በባንኩ የሚገኙት ከ15 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የካርድ ደንበኞች የቪዛ ካርድ ተጠቃሚዎች መሆናቸውን አመልክተዋል።

አቶ ሚደቅሳ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቪዛ ዴቢት እና ዓለም አቀፍ የቅድመ ክፍያ ካርድ ተጠቃሚዎች ከ1 ሺ ብር / 50 ዶላር ጀምሮ በሚያደርጉት እያንዳንዱ ግብይት ይህን እድል ማሸነፍ እንደሚችሉ ገልፀው፣ መልካም እድል ተመኝተዋል።

በቪዛ የምስራቅ አፍሪካ ክላስተር ኃላፊ እና በኢትዮጵያ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ያሬድ እንዳለ በበኩላቸው አጋጣሚው ደንበኞች በዓለም ላይ በከፍተኛ ድባብ ከሚታዩ ሁነቶች አንዱ እና ለብዙዎች በህይወት ዘመን አንዴ የሚገኝ ክስተት የሆነውን የፊፋ ዓለም ዋንጫ ውድድርን በአካል ተገኝተው እንዲመለከቱ ዕድል እንደሚሰጥ ተናግረው፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር ለደንበኞች ይህን ሽልማት በማቅረባቸው ደስተኞች መሆናቸውን ተናግረዋል።

አቶ ያሬድ አሸናፊዎች እያንዳንዳቸው ከሚመርጡት ተጨማሪ አንድ ወዳጃቸው ጋር የጨዋታ ትኬት፣ የአራት ቀናት ማረፊያ፣ በጉዞ ወቅት የሚያደርጉትን የጉብኝት ወጭ ጨምሮ የተለያዩ ስጦታዎች እንደሚበረከትላቸው ገልፀዋል።
16
👍 8
1 1 25K

Обсуждение 1

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Commercial Bank of Ethiopia - Official

198.1K
Commercial Bank of Ethiopia is the leading bank in Ethiopia, established in 1942. Pioneer to introduce modern banking to the country with 1,971 branches and service outlet across the country.
@ www.facebook*.com/combanketh
@ www.twitter.com/combankethiopia
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram