avatar
Commercial Bank of Ethiopia - Official
@combankethofficial
01.04.2026 00:14
“ተግተን እናገለግላለን፤ በፍቅር እናጋራለን!” በሐዋሳ ዲስትሪክት ተካሄደ
****
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሐዋሳ ዲስትሪክት መጪውን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ ለሐዋሳ ከተማ ነዋሪዎች የማዕድ ማጋራት መርሐ - ግብር አካሄዷል፡፡

መርሐ - ግብሩ “ተግተን እናገለግላለን፤ በፍቅር እናጋራለን!” በሚል መሪ ቃል የተከናወነ ሲሆን በከተማው አስተዳደር ለተለዩ ለ200 ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች 25 ኪሎ ስንዴ ዱቄት፣ አምስት ሊትር ፈሳሽ ዘይት እና የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የሲዳማ ክልል መንግስት መስተዳደር ጽ/ቤት ተወካይ እና የመልካም አስተዳደርና ቅሬታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አማረ አላንቦ፤ ባንካችን ለአገራችን ኢኮኖሚ ዕድገት እየተጫወተ ካለው ሚና ባሻገር ማህበረሰባችን ዋጋ ለሚሰጣቸው ሀይማኖታዊ በዓላት አብሮነትን እና በጎነትን ባሕል ለማድረግ እያሳየ ያለው አርአያነት ለሌሎችም ምሳሌ የሚሆን ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደቡባዊ ሪጅን ምክትል ፕሬዚደንት አቶ ፍጹም አላሎ በበኩላቸው፤ ባንካችን በአገራችን ለሚከናወኑ እና የህብረተሰባችንን ሕይወት ለሚያሻሽሉ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ አረጋግጠዋል፡፡

በያዝነው ዓመትም ባንካችን ከ90 ሚሊየን ብር በላይ በመመደብ በሁሉም ዲስትሪክቶች በበዓላት ወቅት ማዕድ በማጋራት ለህብረተሰባችን ያለንን አብሮነትና አጋርነት እያሳየን እንገኛለን ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ልዩ አማካሪ አቶ መከተ ተሰማ መርሐ -ግብሩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ባንካችን ለከተማው ነዋሪዎች እያቀረበ ባለው የባንክ አገልግሎት የነዋሪዎችን ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉን ጠቁመዋል፡፡

የባንካችን ሠራተኞችም የከተማውን ነዋሪ በቅልጥፍና፣ በታማኝነት እና በቅንንነት ስለሚያገለግሉም እናመሰግናለን ብለዋል፡፡ እንደ አገራችን እና አካባቢያችን ባህል በበዓላት ወቅት ድጋፍ ለሚሹ ወገኖቻችን ማዕድ በማጋራት ባንካችን በየጊዜው ለሚያሳየው ፍቅር እና አብሮነት አድናቆታቸውን ቸረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሐዋሳ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ወይሳ ጥላሁን፤ ባንካችን ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እና የህብረተሰባችንን ችግሮች ለማቃለል የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ባንካችን የተቋቋመበትን ዓለማ ለማሳካትም ተግተን እንሰራለን፤ ለማህበረሰባችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ቀድሞ ደራሽ በመሆን ከጎን እንቆማለን በማለት አስገንዝበዋል፡፡ ዲስትሪክቱ ያከናወነው የማዕድ ማጋራት መርሐ - ግብር ለህዝባችን ያለንን ፍቅር እና አገልጋይነት ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
14
👏 1
1 12.6K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Commercial Bank of Ethiopia - Official

198.1K
Commercial Bank of Ethiopia is the leading bank in Ethiopia, established in 1942. Pioneer to introduce modern banking to the country with 1,971 branches and service outlet across the country.
@ www.facebook*.com/combanketh
@ www.twitter.com/combankethiopia
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram