avatar
Commercial Bank of Ethiopia - Official
@combankethofficial
31.03.2026 17:41
እንዴት የሞባይል ባንኪንግ ‘QR’ አገልግሎትን ተጠቅመው ገንዘብ መቀበል/ክፍያ መፈፀም ይችላሉ?
====

1. ገንዘብ ላኪውና ተቀባዩ በተመሳሳይ ቦታ የሚገኙ ከሆነ

• ገንዘብ ተቀባዩ በሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያው ላይ የሚገኘውን የ ‘QR’ ኮድ ምልክት ይጫኑ፤
• ‘ገንዘብ ለመቀበል’ ‘Receive Money’ የሚለውን ይምረጡ፤
• የሚቀበሉትን ገንዘብ መጠን እና ምክንያቱን አስገብተው ‘ቀጥል’ ‘Continue’ የሚለውን ይጫኑ፤
• የሚመጣሎትን የQR ኮድ ወይም ምስል አዘጋጅተው ይጠብቁ፤
• ገንዘብ ላኪው በሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያው ላይ የሚገኘውን የ ‘QR’ ኮድ ምልክት ይጫኑ፤
• ‘ስካን ኪው አር’ ‘Scan QR’ የሚለውን ይምረጡ፤
• ገንዘብ የሚልኩልት ሰው ስልክ ላይ ያለውን QR ኮድ ስካን ያድርጉ፤
• የሚላከውን የገንዘብ መጠን እና ምክንያት በማረጋገጥ ገንዘብ በቀላሉ መላክ ይቻላል፡፡

2. ገንዘብ ላኪውና ተቀባዩ አንድ ላይ የማይገኙ ሲሆን

• ገንዘብ ተቀባዩ በሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያው ላይ የሚገኘውን የ ‘QR’ ኮድ ምልክት ይጫኑ፤
• ‘ገንዘብ ለመቀበል’ ‘Receive Money’ የሚለውን ይምረጡ፤
• ‘የገንዘብ መጠን እና ምክንያት’ ‘Amount and Reason’ የሚለውን ይምረጡ፤
• የገንዘብ መጠን እና ምክንያቱን አስገብተው ‘ቀጥል’ ‘Continue’ የሚለውን ይጫኑ
• ‘ያጋሩ’ ‘Share’ የሚለውን ይጫኑ፣
• ‘በማስፈንጠሪያ መልክ ያጋሩ’ ‘Share as a link’ የሚለውን ተጭነው ‘እሺ’ ‘Ok’ የሚለውን ይምረጡ፣
• በSMS፣ በቴሌግራም እና በሌሎችም መንገዶች ተጠቅመው ማስፈንጠሪያውን ለገንዘብ ላኪው ይላኩ፣
• ገንዘብ ላኪው በመልእክት የደረሰውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመክፈት የገንዘብ መጠን እና ምክንያት አረጋግጦ ገንዘብ ማስተላለፍ ይችላል፡፡

#CBE
37
👏 2
👍 1
3 7 15.1K

Обсуждение 3

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Commercial Bank of Ethiopia - Official

198.1K
Commercial Bank of Ethiopia is the leading bank in Ethiopia, established in 1942. Pioneer to introduce modern banking to the country with 1,971 branches and service outlet across the country.
@ www.facebook*.com/combanketh
@ www.twitter.com/combankethiopia
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram