avatar
Commercial Bank of Ethiopia - Official
@combankethofficial
30.03.2026 18:12
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ55ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ሻምፒዮና አሸናፊ ሆነ፡፡
• የባንኩ አትሌቲክስ ቡድን ከሰበራቸው 6 ሪከርዶች አንዱ ለ30 ዓመታት ተይዞ የቆየ ነው፡፡
**************
በአደይ አበባ ስታዲየም ከመጋቢት 15 ቀን እስከ መጋቢት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ሲካሄድ በቆየው 55ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አትሌቲክስ ቡድን በሴት፣ በወንድ እና በአጠቃላይ ውጤት የተዘጋጁትን ሶስቱንም ዋንጫዎች በመውሰድ ሻምፒዮን ሆኗል።

የባንኩ አትሌቲክስ ቡድን በውድድሩ 6 ሪከርዶችን ሲሰብር፣ በሴቶች የ400 ሜትር መሰናክል የተሰበረው ሪከርድ ላለፉት 30 ዓመታት ተይዞ የቆየ ነው፡፡

በውድድሩ የመጨረሻ ቀን በተደረገ የ4 በ400 ሜትር የዱላ ቅብብል ፍፃሜ የባንኩ አትሌቲክስ ቡድን ውድድሩን በ3:03፡45 ሰዓት በመጨረስ አዲስ የኢትዮጵያ ክብረ ወሰን ያስመዘገበ ሲሆን፣ በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና መሳተፍ የሚያስችል ሚኒማ ማሟላትም ተችሏል፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን ፤ አትሌት መሠረት ደፋር እና ሌሎች የፌዴሬሽኑ የስራ ኃላፊዎች በውድድር ስፍራው በመገኘት ለአሸናፊዎች ሽልማት ሰጥተዋል።

ጥሩ ውጤት ያስመዘገቡ የባንኩ አትሌቲክስ ቡድን አባላት ኢትዮጵያን በመወከል በጋና አዘጋጅነት በሚካሄደው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻሚፒዮና ላይ እንደሚሳተፉም ይጠበቃል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አትሌቲክስ ቡድን በተመሳሳይ 54ኛዉን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በበላይነት ማጠናቀቁ ይታወቃል።

በተገኘው ድል የባንኩን አትሌቶች፣ የቡድኑን አሰልጣኞች እና ቡድን መሪ፣ ደጋፊዎች እና መላዉን የባንካችንን ማሕበረሰብ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን፡፡
53
👏 16
😁 2
12 5 15.1K

Обсуждение 12

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Commercial Bank of Ethiopia - Official

198.1K
Commercial Bank of Ethiopia is the leading bank in Ethiopia, established in 1942. Pioneer to introduce modern banking to the country with 1,971 branches and service outlet across the country.
@ www.facebook*.com/combanketh
@ www.twitter.com/combankethiopia
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram