avatar
Commercial Bank of Ethiopia - Official
@combankethofficial
30.03.2026 15:53
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለጋሞ ዞን የተፈጥሮ አደጋ ተጎጂዎች 11.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡
===========
ባንካችን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ በተከሰተው የተፈጥሮ አደጋ ጉዳት ለደረሳባቸው ወገኖቻችን 11.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

በድጋፍ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደንበኞች አገልግሎት ም/ኘሬዚዳንት አቶ ኃይለየሱስ በቀለ ባንካችን ጉዳቱ በደረሰበት ወቅት በቦታው በመገኘት ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብቶ እንደነበር አስታውሰው ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

ከተሰጠው ድጋፍ ውስጥ የባንካችን ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት አንድ ሚሊዮን ብር ያበረከተ ሲሆን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሠራተኞች ማህበር ደግሞ በማህበሩ ፕሬዚዳንት አቶ አበራ ጌታቸው በኩል 500 ሺህ ብር አበርክቷል፡፡

የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ደምሴ አድማሱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባደረገው ድጋፍ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው ሌሎች ተቋማትም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን አርዓያነት መከተል አለባቸው ብለዋል፡፡

በስነስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደቡብ ሪጅን ም/ኘሬዝደንት አቶ ፍፁም አላሎ፣ የጋሞ አባቶች እና ሌሎችም የባንካችን የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
32
👍 15
👏 11
9 1 14.6K

Обсуждение 9

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Commercial Bank of Ethiopia - Official

198.1K
Commercial Bank of Ethiopia is the leading bank in Ethiopia, established in 1942. Pioneer to introduce modern banking to the country with 1,971 branches and service outlet across the country.
@ www.facebook*.com/combanketh
@ www.twitter.com/combankethiopia
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ
Открыть в Telegram