Hijra Bank @HijraBank 09.03.2026 14:02 Скопировать Пожаловаться #ባህርዳር #Bahardaar ሂጅራ ባንክ ከአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጋር በመተባበር የሰደቃ መረኃ-ግብር አካሄደ። ሂጅራ ባንክ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል "ረመዷን የሰደቃ እና የእዝነት ወር" በሚል መሪ ቃል እያካሄደ የሚገኘው የተቀናጀ መረኃ-ግብር በመቀጠል በአማራ ክልል መዲና ውቢቷ ባህርዳር ለሚገኙ ዑለሞች ድጋፉን አድርጓል። በመረኃ-ግብሩ ላይ የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ምክርቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ኑረዲን ቃሲምን ጨምሮ የባንኩ የስራ ሃላፊዎች እና በከተማዋ የሚገኙ ዑለማኦች ተሳታፊ ሆነዋል። ሙሉ ለሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ለደንበኞቹ ለማቅረብ እየተንቀሳቀሰ ያለው ሂጅራ ባንክ ማህበራዊ ሀላፊነቱን ለመወጣት በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል። ሂጅራ ባንክ! ጉዞ ወደ ብሩህ ተስፋ! ❤ 8 2.1K
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram