Ethiopian News Agency @EthiopianNewsA 09.04.2026 22:36 Скопировать Пожаловаться ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የቡሩንዲው ፕሬዝዳንት ኢቫሪስቴ ንድያይሺሚዬ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተለያዩ የመግባቢያ ስምምነቶች ልውውጥ ላይ ታድመዋል። በመከላከያ፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በውሃና ኢነርጂ፣ በግብርና ፣ በንግድ ፣ በዲጂታል መታወቅያ እና በቱሪዝም ዘርፎች የተፈረሙት እነዚህ ሁሉን አቀፍ ስምምነቶች ለቀጣናዊ ዘላቂ ልማት ያለውን የጋራ ቁርጠኝነት በይፋ የሚያረጋግጡ ናቸው። እነዚህ የመግባቢያ ስምምነቶች የሁለቱን ሀገራት ሰፊ አቅም በመደመር ወደ ብልጽግና ለምናደርገው የጋራ ጉዞ መሠረት የሚጥሉ ናቸው። #PMOEthiopia ❤ 1 1.2K
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram