avatar
Ethiopian News Agency
@EthiopianNewsA
15.04.2026 14:54
የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ሀገራችን በምግብ ራሷን ለመቻል የጀመረችው ጉዞ በተግባር ስር እየሰደደ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው -ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 7/2018 (ኢዜአ)፦ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን ለመቻል የጀመረችው ጉዞ በተግባር ስር እየሰደደ መሆኑን እንደሚያረጋግጥ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ አሎማ ክላስተር በበጋ መስኖ የለማውን የደረሰ የስንዴ ማሳ ተመልክተዋል።

የመደመር መንግሥት ለበጋ መስኖና ለስንዴ ምርታማነት የሰጠው ትኩረት የዜጎችን ሕይወት እየቀየረና የሀገርን የምግብ ሉዓላዊነት እያረጋገጠ እንደሚገኝም በመልዕክታቸው ጠቁመዋል።

ዛሬ የተመለከትነው የስንዴ ልማትም የራዕያችንን ውጤት፣ የሀሳባችን መሬት መንካትና ፍሬ የማግኘታችን ተጨባጭ ማሳያ ነው ብለዋል።

አርሶ አደሩን በተደመረ አቅም በማትጋትና የተፈጥሮ ፀጋዎቻችንን በመጠቀም በሁሉም መስክ ሀገርን የማሻገር ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።
👍 1
1.2K
avatar
Ethiopian News Agency
@EthiopianNewsA
15.04.2026 14:30
ሦስተኛው የቅርስ ምርምር ጉባዔ ከሚያዚያ 13 ጀምሮ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 7/2018 (ኢዜአ)፦ "የኢትዮጵያ ቅርስ ምርምር በዲጂታል ዘመን" በሚል መሪ ሀሳብ ሦስተኛው የቅርስ ምርምር ጉባዔ ከሚያዚያ 13 እስከ 14 ቀን 2018 እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን አስታወቀ።

የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኤሊያስ ሽኩር ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፤ ጉባዔው" የኢትዮጵያ ቅርስ ምርምር በዲጂታል ዘመን" በሚል መሪ ሃሳብ ይካሄዳል።

የምርምር ጉባዔው በቅርስ ልማት ዘርፍ ያሉ ተግዳሮቶችን መርምሮ መፍትሄ ለመስጠት፣ አዳዲስ እውቀቶችን ለመለዋወጥ እና የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዚህ የምርምር ጉባዔ ላይ 13 አዳዲስ የምርምር ጹሁፎች እንደሚቀርቡ ተናግረው፤ ጉባዔው የሚካሄደው በኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን አዳራሽ መሆኑንም አስታውቀዋል።
4
2 1.5K
avatar
Ethiopian News Agency
@EthiopianNewsA
15.04.2026 12:48
"አምራች ኢንዱስትሪ ለመለወጥ ለማደግ ለሚያስብ ሀገር ሁሉ በጣም ወሳኝ ነገር ነው:: የኢኮኖሚ ልብ ነው።" -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
#PMOEthiopia
2
1 1.5K
avatar
Ethiopian News Agency
@EthiopianNewsA
15.04.2026 08:14
ወሎ የብዝኃነት እና የአብሮነት ተምሳሌት ናት - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 7/2018 (ኢዜአ)፦ ወሎ የብዝኃ ሃይማኖትና ባህል መገኛ፣ የፍቅርና የአብሮነት ተምሳሌት እንዲሁም የታሪክ ማህደር ናት ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ወሎ ኮምቦልቻ መግባታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም፣ እንደ ቦርከና ወንዝ የማይነጥፈው የህዝቡ ገራገርነትና የማይጠገበው ትኅትና፣ እንዲሁም እንደ ጦሳ ተራራ የገዘፈው መስተንግዶና ደማቅ አቀባበል ልባቸውን በሐሴት እንደሞላው ገልጸዋል።

በወሎ ኮምቦልቻ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ላደረጉላቸውና አርሂቡ ብለው ለተቀበሏቸው ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር፣ ለክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ ለሃይማኖት አባቶች፣ ለሀገር ሽማግሌዎች እና ለመላው የወሎ ሕዝብ ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Ethiopian News Agency #ኢዜአ
4
😁 1
3 1.4K
avatar
Ethiopian News Agency
@EthiopianNewsA
15.04.2026 10:14
የሉዓላዊነት ልብ
ዛሬ ከምሽቱ 2:30 ይጠብቁ።

ክፍል 2
123
avatar
Ethiopian News Agency
@EthiopianNewsA
15.04.2026 09:52
195
avatar
Ethiopian News Agency
@EthiopianNewsA
15.04.2026 08:22
1 312
avatar
Ethiopian News Agency
@EthiopianNewsA
15.04.2026 08:18
1 287
avatar
Ethiopian News Agency
@EthiopianNewsA
14.04.2026 22:51
6
1 750
avatar
Ethiopian News Agency
@EthiopianNewsA
14.04.2026 22:47
ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 6/2018 (ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የላይቤሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ ከሁለትዮሽ ስብሰባቸው ቀጥሎ ሁለት የመግባቢያ ስምምነቶች ልውውጥ ላይ ተገኝተዋል።

እነዚህ ስምምነቶች በትምህርት፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ በማተኮር ለወደፊት ትብብራችን እንደ ስትራቴጂካዊ መሠረት እና ተግባራዊ ፍኖተ-ካርታ እንደሚያገለግሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

የትብብር ማዕቀፉ፤ ኢትዮጵያ እና ላይቤሪያን በመደመር መርህ በማጣመር ለአኅጉራዊ ትስስር ዋነኛ አንቀሳቃሽ ኃይል ከመሆኑም ባለፈ፣ የአፍሪካ ሀገራት በእውነተኛ ትብብር ምን ሊያሳኩ እንደሚችሉ እንደ ታላቅ ተምሳሌት የሚጠቀስ መሆኑም ተገልጿል።
3
1 557
avatar
Ethiopian News Agency
@EthiopianNewsA
14.04.2026 21:15
የላይቤሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳራ ቤይሶሎው ኒያቲ በ EAI ያደረጉት ጉብኝት

#Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
693
avatar
Ethiopian News Agency
@EthiopianNewsA
14.04.2026 20:29
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የላይቤሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ፣ በወዳጅነት እና በጋራ መከባበር ላይ መሠረት ያደረገውን ግንኙነት ወደ ላቀ ምዕራፍ ለማሸጋገር ያላቸውን የጸና አቋም በማረጋገጥ ሰላምታ ተለዋውጠዋል።
#PMOEthiopia
👍 2
1
691

Ethiopian News Agency

21.3K
Ethiopian News Agency official telegram channel
Открыть в Telegram