avatar
Ethiopian News Agency
@EthiopianNewsA
09.04.2026 15:00
ኢትዮ ቴሌኮም "ቶሎ" የተሰኘ የፈጣን መንገድ የክፍያ ሥርዓት በቴሌብር አስጀመረ

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 1/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮ ቴሌኮም "ቶሎ" የተሰኘ የፈጣን መንገድ የክፍያ ሥርዓትን በቴሌ ብር አገልግሎት መስጠት የሚያስችለውን ዲጂታል የክፍያ ስርአት ስራ አስጀመረ።

ኢትዮ ቴሌኮም "ቶሎ" የተሰኘው የክፍያ ስርአት የማስጀመር መርሀ ግብር አካሂዷል።

ኢትዮ-ቴሌኮም ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ አገልግሎቶችን እያስተዋወቀ መሆኑን በወቅቱ ተገልጿል።

ኢትዮ-ቴሌኮም ከመደበኛ የቴሌኮም አገልግሎት ባሻገር ቀልጣፋ፣ምቹና ወጪ ቆጣቢ አገልግሎት በማቅረብ የፋይናንስ ዘርፉን እየደገፈ መሆኑንም የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ አስረድተዋል።

በዚህም የሀገረን ልማት ዘላቂና አካታች ለማድረግ ዲጂታል መሰረተ ልማት ዝርጋታ ላይ ትኩረት በማድረግ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቅሰዋል።
2 1.1K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopian News Agency

21.3K
Ethiopian News Agency official telegram channel
Открыть в Telegram