avatar
Ethiopian News Agency
@EthiopianNewsA
07.04.2026 14:40
አምባሳደር ቆንጂት በዲፕሎማሲው መስክ በብልህ አመራራቸውና በጽኑ ማንነታቸው ሁሌም ይታወሳሉ-ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ አንጋፋዋ ዲፕሎማት አምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ በማረፋቸው የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል።

አምባሳደሯ በዲፕሎማሲው መስክ ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ላበረከቱት ጉልህ አስተዋጽኦ፣ ለሰጡት አስተምህሮና ለነበራቸው ብልህ አመራር ምንጊዜም ሲታወሱ እንደሚኖሩ ፕሬዝዳንት ታዬ በመልዕክታቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።

ፕሬዝዳንቱ አምባሳደሯን ሲገልጹ ትጉህና ከብረት የጠነከሩ ዲፕሎማት ነበሩ በማለት፣ ለሙያቸው የነበራቸውን ጽኑ አቋምና የሀገር ፍቅር ስሜት አድንቀዋል።

ፕሬዝዳንት ታዬ በአምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ ህልፈት ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለመላው የዲፕሎማሲው ማህበረሰብ መጽናናትን ተመኝተዋል።
1
1 980

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopian News Agency

21.3K
Ethiopian News Agency official telegram channel
Открыть в Telegram