Ethiopian News Agency @EthiopianNewsA 07.04.2026 14:18 Скопировать Пожаловаться ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ አዲስ አበባ፤መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአምባሳደር ቆንጂት ስነጊዮርጊስ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ታሪክ ውስጥ የማይረሳ እና ታላቅ ዐሻራን ማሳረፍ የቻሉት አምባሳደር ቆንጂት ሥነጊዮርጊስ ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው ጥልቅ ሐዘን ተሰምቶኛል ብለዋል። አምባሳደር ቆንጂት እስከ ከፍተኛ ዲፕሎማትነት በደረሰ ረጅም የሥራ ዘመናቸው ለሀገራችን ብሔራዊ ጥቅም ያስመዘገቡት ድል እና ያበረከቱት አስተዋጽዖ ሁልጊዜም በክብር የሚታወስ መሆኑን ገልጸዋል። አምባሳደር ቆንጂት ለኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ከነበራቸው አበርክቶ ባለፈ ለሴት ዲፕሎማቶችም የጽናት እና የጥንካሬ ተምሳሌት ነበሩ ነው ያሉት። ፈጣሪ ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑር ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን፥ ለቤተሰቦቻቸው፣ለሥራ ባልደረቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ 896
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram