avatar
Ethiopian News Agency
@EthiopianNewsA
07.04.2026 13:23
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ ኅልፈተ ሕይወት የተሰማቸውን ኀዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፤መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ ኅልፈት ሕይወት የተሰማቸውን ኀዘን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ኢትዮጵያን በዲፕሎማሲው መስክ ያገለገሉት አምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ በማረፋቸው የተሰማኝን ኀዘን ለመግለጽ እወዳለሁ ብለዋል።

አምባሳደር ቆንጂት ከልጅነት እስከ ዕውቀት ኢትዮጵያን በዲፕሎማትነት በማገልገል፣ ከአምባሳደር ዮዲት እምሩ ቀጥለው ሁለተኛዋ ሴት የኢትዮጵያ አምባሳደር መሆናቸውን አውስተዋል።

ለሕግ፣ ለአሠራር፣ ለፕሮቶኮል እና ለኢትዮጵያ ጥቅሞች በነበራቸው የጸና አቋም እናስታውሳቸዋለን ብለዋል።

ከእርሳቸው በኋላ አያሌ ሴት ዲፕሎማቶች በመስኩ እንዲሠማሩ መንገዱን ማስፋታቸውንም አመልክተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለሥራ ባልደረቦቻቸው እና ለመላ ኢትዮጵያውያን መጽናናትን ተመኝተዋል።

#Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
3
1.1K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopian News Agency

21.3K
Ethiopian News Agency official telegram channel
Открыть в Telegram