የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በዓለም አቀፍ ደረጃ ይፈለግ የነበረ አደገኛ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ ይትባረክ ዳዊት (ክብሮም)ን ከነግብረ-አበሮቹ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 28 /2018(ኢዜአ)፦ ከ3 ሺህ በላይ ሰዎችን በሕገ-ወጥ መንገድ በማዘዋወር፣ ከ100 በላይ ሰዎችን ለሞት የዳረገ እና ከ50 በላይ ሴቶች እንዲደፈሩ ያደረገው ይትባረክ ዳዊት (ክብሮም)ን ከ9 ግብረ-አበሮቹ ጋር በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ አጠናቆ ለዓቃቢ ህግ መላኩን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለኢዜአ በላከው መረጃ ይህንን ውስብስብና ድንበር ተሻጋሪ የወንጀል ምርመራ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል ከሚሰራ The Regional Operational Centre in support of the Khartoum process (ROCK) ከተባለ ድርጅት ጋር ባደረገው የመረጃ ልውውጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ይፈለግ የነበረው አደገኛ ህገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ ይትባረክ ዳዊት አለሙን በትግራይ ክልል ሽሬ ከተማ ላይ ፖሊስ በቅንጅት በቁጥጥር ሥር አውሏል።
ተጠርጣሪው በፓስፖርት ስሙ ይትባረክ ዳዊት አለሙ፣ ቤተሰቦቹ በልጅነቱ ያወጡለት ስም ጳውሎስ ዳዊት ወልዳይ፤ ወንጀል መስራት ሲጀምር የሚታወቅባቸው ስሞች አድሀኖም፣ ሱዳን ሀገር የሚታወቅበት ስም አህመድ፤ ሱማሊያ፣ ጅቡቲ እና ኬንያ የሚጠቀምበት ስም ሙኒር ሲሆን ክብሮም ደግሞ በስዊድን እና በሌሎች የአውሮፓ ሀገራት የሚጠቀምባቸው ሀሰተኛ ስሞች መሆናቸውን ፖሊስ በምርመራው አረጋግጧል፡፡
https://www.ena.et/web/amh/w/amh_8609791
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram