avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
19.02.2026 17:55
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የትግራይ ክልል የምክክር ሂደትን በተመለከተ በአዲስ አበባ ለሚኖሩ እና ከክልሉ ለሚመጡ የማኅበረሰብ ክፍሎች “ከፍተኛ ጥሪ” በማድረግ የምክረ-ሐሳብ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር ለማከናወን ማቀዱን አስታወቀ።

መርሃ ግብሩን በሚቀጥለው ሳምንት መጨረሻ ለማካሄድ መታቀዱን የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

ትላንት ረቡዕ የካቲት 11፤ 2018 በተካሄደው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ላይ የኮሚሽኑን የአራት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት ፕሮፌሰር መስፍን፤ ኮሚሽኑ መድረስ ከነበረበት 1,332 ወረዳዎች እና የከተማ አስተዳደሮች 93 በመቶ በሚሆኑት የህብረተሰብ ተወካዮች በማስመረጥ እና አጀንዳዎችዎችን በማሰባሰብ ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ዝግጁ ማድረጉን አስታውቀዋል።

በዚህ ጊዜ ውስጥ በትግራይ ክልል ተሳታፊ የመለየት ሂደትን ለማጠናቀቅ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም ይህ አለመከናወኑን ዋና ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።

በትግራይ ለማካሄድ የታቀደው የምክክር ሂደት እስኪሳካ ድረስ በእቅድ የተያዘው፤ በቀጣዩ ሳምንት “ከፍተኛ ጥሪ” በማድረግ በአዲስ አበባ ከተማ የምክረ-ሐሳብ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር ማካሄድ መሆኑን አመልክተዋል።

በዚህ መርሃ ግብር የሚሳተፉት በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች እና ከትግራይ ክልል የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ተወካዮች እንደሆኑም አስረድተዋል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17474/

@EthiopiaInsiderNews
8
👎 2
🤮 2
😁 1
3 6.8K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram