ቪዲዮ፦ ዛሬ ረቡዕ የካቲት 11፤ 2018 በነበረው አስቸኳይ ስብሰባቸው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንን የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ያደመጡት የፓርላማ አባላት፤ በትግራይ ሊካሄድ ታቅዶ ስለዘገየው የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ጥያቄ ሰንዝረዋል።
የኢዜማው ዶ/ር አብርሃም በርታ፤ በትግራይ ክልል ውስጥ ምክክሩ እንዳይደረግ “ተጽዕኖ እየፈጠረ ያለው” ማን እንደሆነ ጠይቀዋል።
ክልሉ የምክክሩን ሂደት እንዳይከናወን የተደረገው፤ “በህገ ወጥ ቡድኑ፣ በምርጫ ቦርድ በተሰረዘው ህወሓት፤ ተጠልፎ፣ ተጠርንፎ ተይዞ ነው [ወይ]?” ሲሉም ተጨማሪ ጥያቄ አክለዋል። “ይሄ ከሆነ የፌደራል መንግስትም ትልቅ ኃላፊነት አለበት። ለጊዜያዊ አስተዳደሩ ብቻ የሚተው አይደለም” ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሂሩት ገብረሥላሴ፤ የትግራይ ጉዳይ “ረጅም ጊዜ እንደወሰደባቸው” አምነዋል። ኮሚሽኑ በምክክር ሂደቱ ወቅት በሌሎች ክልሎች በአማካኝ ሶስት ጊዜ ግንኙነት እንደሚያደርግ የጠቀሱት ምክትል ኮሚሽነሯ፤ በትግራይ ክልል ግን 20 engagement ማድረጋቸውን በአጽንኦት አንስተዋል።
“ትግራይ ውስጥ engage እያደረግን ሃሳብ እየተለዋወጥን ነው የቆየነው። ትግራይ ውስጥ ምንም ስራ አልተሰራም ማለት አይቻልም። ከሌላ ክልል በበለጠ ብዙ ለፍተናል” ሲሉም ኮሚሽነር ሂሩት ሁኔታውን አስረድተዋል።
ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል የያዘው እቅድ እንዳልተሳካ ያመለከቱት ምክትል ኮሚሽነሯ፤ የአጀንዳ ማሰባሰቡን ለማካሄድ ሌላ አማራጭ እንደሚከተል ተናግረዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
🔴የትግራይ ክልል የምክክር ሂደትን በተመለከተ የቀረበውን ጥያቄ እና ምላሽ ለመመልከት ይህን ሊንክ ይጫኑ➡️
https://youtu.be/oKi0uenvdfY
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram