avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
18.02.2026 22:16
ቪዲዮ፦ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የስራ ዘመን በተራዘመበት በዛሬው የፓርላማ አስቸኳይ ስብሰባ ላይ ከተነሱ ጥያቄዎች መካከል በእስር ላይ የሚገኙ “የአማራ ልሂቃንን” የተመለከተው ይገኛል። በዚህ ስብሰባ ላይ ጥያቄ ካነሱ የፓርላማው አባላት መካከል ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ አንዱ ናቸው።

ዶ/ር ደሳለኝ የህዝብ እንደራሴዎችን ጨምሮ በእስር ላይ የሚገኙ “የአማራ ልሂቃን እንዲፈቱ በእናንተ በኩል ጥያቄ አቅርባችሁ አስፈጻሚው አካል ምንም ያደረገው ነገር የለም” ብለዋል። ይህንን ሁኔታ “ለሚዲያም፣ ለኢትዮጵያ ህዝብም ስታሳውቁ አላያችሁም” በማለት ኮሚሽነሮቹን ተችተዋል።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሂሩት ገብረሥላሴ ለጥያቄው በሰጡት ምላሽ፤ “የእኛ ጥረት በዘር ሳይሆን በአጠቃላይ የሰው ልጆች መብት ተከብሮ፤ ያለአግባብ መታሰር ከሌለባቸው መታሰር እንደሌለባቸው ግፊት እናደርጋለን” ብለዋል። መንግስት እርምጃ አለመውሰዱን “ለምን አላጋለጣችሁም” ለሚለው ግን “እኛ አክቲቪስቶች አይደለንም” ሲሉ መልሰዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

🔴የዶ/ር ደሳለኝን ጥያቄ እና የኮሚሽነር ሂሩትን ምላሽ ለመመልከት ይህን ሊንክ ይጫኑ https://youtu.be/8_T8KgBpU3A

@EthiopiaInsiderNews
5
👍 1
7 5.8K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram