avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
18.02.2026 19:41
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንን የስራ ዘመን በስምንት ወር አራዘመ። ፓርላማው የኮሚሽኑን የስራ ዘመን ለሁለተኛ ጊዜ ያራዘመው፤ ዛሬ ረቡዕ የካቲት 11፤ 2018 ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ነው።

በታህሳስ 2014 ዓ.ም በወጣ አዋጅ የተቋቋመው ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ፤ መጀመሪያ የተሰጠው የሶስት ዓመት የስራ ዘመን ነበር። ኮሚሽኑ በተሰጠው ጊዜ ስራውን ማገባደድ ባለመቻሉ፤ በየካቲት 2017 ዓ.ም. ተመሳሳይ ሁኔታ በተካሄደ አስቸኳይ የፓርላማ ስብሰባ አንድ ዓመት እንደተጨመረለት ይታወሳል።

የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለዕረፍት ከተበተኑበት ተጠርተው ባካሄዱት በዛሬው አስቸኳይ ስብሰባ፤ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የአራት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦላቸው ውይይት አድርገውበታል። ውይይቱን ተከትሎ የምክር ቤቱ የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ ያደመጡት የፓርላማ አባላቱ፤ የኮሚሽኑን የስራ ዘመን ለሁለተኛ ዙር እንዲራዘም በሙሉ ድምጽ ወስነዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17465/

@EthiopiaInsiderNews
10
😁 3
👍 1
👏 1
4 6.1K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram