ገነት ተስፋሁን በአዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፊጋ አካባቢ በግለሰብ ቤት ተቀጥራ የምትሠራ ወጣት ናት። ለሳምንት ፍጆታ የሚውል አትክልት እንድትገዛ ባለፈው እሁድ ረፋድ ላይ በአካባቢው አደባባይ ዙሪያ ወደሚገኘው “የእሁድ ገበያ” ትላካለች።
የእቃ መያዣ ሳትይዝ ከቤት የወጣችው ገነት፤ ከረጢት መሰል ነገር ወደ ወደሚሸጡ ነጋዴዎች ተጠግታ ዋጋውን ስትጠይቅ የተሰጣት ምላሽ ወደ መጣችበት እንድትመለስ አስገድዷታል። እንዲህ አይነት ነገር ሲገጥማት በጥቂት ብሮች ታገኘው የነበረው ፌስታል በመታገዱ ምክንያት፤ በምትኩ በገበያ ላይ ያለው በ“ስስ ማዳበሪያ” የተሠራ የእቃ መያዣ ነው።
የእዚህን መሰል እቃ መያዣዎች አነስተኛ የመሸጫ ዋጋ 60 ብር መሆኑ ሲነገራት፤ ወደ ቤት ተመልሳ ይህንኑ ለአሠሪዎቿ ማሳወቅ ነበረባት። ምርጫ ያልነበራቸው አሠሪዎቿ ለእቃ መያዣ ተጨማሪ ገንዝብ ከሰጧት በኋላ ነበር ወደ ገበያ ተመልሳ አትክልት መሸመት የቻለችው።
ቦሌ ወደ ሚገኘው ሰን ሲቲ ሱፐርማርኬት ከትላንት በስቲያ ሰኞ ያቀናው አብነት ሲሳይ፤ ፌስታል በመከልከሉ ምክንያት ለገዛው ቆሎ እና ውሃ በመያዣነት የቀረበለት አማራጭ ካርቶን ብቻ መሆኑ አላስደሰተውም።
“የሽያጭ ባለሙያዎቹ እቃ መያዣ እንዳለኝ ከጠየቁኝ በኋላ እንዳልያዝኹ ስነግራቸው ካርቶን እንድጠቀም ጠይቀውኝ ነበር” የሚለው አብነት፤ ካርቶኑ ትልቅ እና ለመያዝ አመቺ ባለመሆኑ ከሱፐር ማርኬቱ የገዛውን ቆሎ እና ውሃ በእጁ ይዞ መውጣቱን መርጧል።
🔴ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2026/17454/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram