avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
17.02.2026 15:53
በዘንድሮው በጀት ዓመት ስድስት ወራት ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወደ ማዕከላዊው ብሔራዊ ባንክ የገባው የወርቅ መጠን፤ ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር ከእጥፍ በላይ ብልጫ ማሳየቱ ተገለጸ።

ብሔራዊ ባንክ ለወርቅ አቅራቢዎች የሚከፍለውን ማበረታቻ ማሳደጉ፤ ለክልሉ የወርቅ አቅርቦት መጨመር በዋና ምክንያትነት ተጠቅሷል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2018 በጀት ዓመት ስድስት ወራት ውስጥ ከልዩ አነስተኛ እና ባህላዊ ወርቅ አምራቾች ለመሰብሰብ ያቀደው 3,525 ኪሎ ግራም ወርቅ ነበር።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን ከትላንት በስቲያ እሁድ ለክልሉ ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት፤ በመንፈቅ ዓመት ውስጥ ለብሔራዊ ባንክ የገባው የወርቅ መጠን 4,158.6 ኪሎ ግራም እንደሆነ አስታውቀዋል።

ይህ አኃዝ ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ወደ ብሔራዊ ባንክ ከገባው 1,697.68 ኪሎ ግራም ወርቅ ጋር ሲነጻጸር ከእጥፍ በላይ ጭማሪ ያሳየ መሆኑን የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ቱጃኒ አዳም ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

ብሔራዊ ባንክ ለወርቅ አቅራቢዎች የሚከፍለውን ማበረታቻ ማሳደጉ ተከትሎ፤ አምራቾች ምርታቸውን ወደ ህጋዊ መስመር በማስገባታቸው የክልሉ የወርቅ አቅርቦት መጨመሩን ኃላፊው አስረድተዋል። 

ብሔራዊ ባንክ ባለፈው ጥቅምት ወር ላይ ባሻሻለው የወርቅ ግዢ መመሪያ፤ ለባንኩ የሚቀርበው የወርቅ መጠን ከአምስት ኪሎ ግራም በላይ ከሆነ ከዓለም አቀፍ ዋጋ ላይ 15 በመቶ ጭማሪ በማድረግ እንደሚገዛ አስታውቆ ነበር።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17405/

@EthiopiaInsiderNews
7
🍌 1
1 5.9K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram