avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
17.02.2026 00:54
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከዚህ ቀደም የጸጥታ መደፍረስ ከነበረባቸው ከጋሞ እና ጋርዱላ ዞኖች የመከላከያ ሰራዊት ለቅቆ መውጣቱን ተከትሎ፤ በስፍራዎቹ አለመረጋጋት መከሰቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ።

የመከላከያ ሰራዊት አካባቢዎቹን ባለፉት ሶስት ቀናት ለቅቆ መውጣቱን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያረጋገጡ አንድ የክልሉ ኃላፊ በበኩላቸው፤ በስፍራዎች በተፈጠረው አለመረጋጋት በሰዎች ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ገልጸዋል።

ከትላንት እሁድ የካቲት 8፤ 2018 ጀምሮ የጸጥታ መደፍረስ ካጋጠማቸው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አካባቢዎች መካከል የጋሞ ዞን አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ እና የጋርዱላ ዞን ደራሼ ወረዳ እንደሚገኙበት ነዋሪዎች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስታውቀዋል።

በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ የሚገኙ አንድ የአካባቢው ነዋሪ፤ የጸጥታ አለመረጋጋት የተፈጠረው የዘይሴ ብሔረሰብ በሚገኝባቸው ቀበሌዎች መሆኑን አመልክተዋል። ትላንት አመሻሽ አካባቢ በተለይ “ዘይሴ ወዘቃ” የተባለ ቀበሌ ላይ የተኩስ ድምጾች ይሰሙ እንደነበር እኚሁ ነዋሪ ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደምም ራስን በራስ ከማስተዳደር ጥያቄ ጋር በተገናኘ በዘይሴ ብሔረሰብ መኖሪያ ቀበሌዎች ግጭቶች እና አለመረጋጋቶች እንደነበሩ የሚናገሩት ነዋሪው፤ የትላንቱ ሁኔታም ከዚሁ ጋር የተገናኘ መሆኑን አስረድተዋል።

በአካባቢው በተፈጠረው አለመረጋጋት እና ተኩስ ምክንያት፤ ከአርባምንጭ – ጊዶሌ – ኮንሶ የሚወስደው አውራ ጎዳና በትላንትናው ዕለት ተዘግቶ እንደነበረ ነዋሪው ተናግረዋል።

የጸጥታ ኃይሎች በአካባቢው ላይ ከደረሱ በኋላ ለጥቂት ሰዓታት ተዘግቶ የነበረው አውራ ጎዳና መከፈቱን ነዋሪው ገልጸዋል።

🔴 ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17398/

@EthiopiaInsiderNews
12
🤔 1
😢 1
13 6.1K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram