የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ለቀጣዩ ምርጫ በዕጩነት ካዘጋጃቸው ተወዳዳሪዎች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ የሺዋስ አሰፋ ከአንድ ቀን እስር በኋላ ተፈቱ።
አቶ የሺዋስ ዛሬ ረቡዕ የካቲት 4፤ 2018 ከቀኑ 10 ሰዓት ገደማ ተፈትተው በስልክ እንዳነጋገሯቸው የኢሕአፓ ፕሬዝዳንት አቶ አብርሃም ሃይማኖት ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።
በተለያዩ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ ለረዥም ጊዜ የፖለቲካ ተሳትፎ ያላቸው አቶ የሺዋስ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት፤ ትላንት ማክሰኞ ከቀኑ 8 ሰዓት ገደማ እንደነበር የኢሕአፓ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ይስሀቅ ወልዳይ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ገልጸዋል።
አቶ የሺዋስ የተያዙት ከመኖሪያ ቤታቸው ውጭ ባለ ስፍራ መሆኑን ኃላፊው አስረድተዋል።
ፖሊስ ፖለቲከኛውን በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና መስሪያ ቤት ወደሚገኘው ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደወሰዳቸው ማረጋገጣቸውን ጉዳዩን ሲከታተሉ የቆዩት አቶ ይስሀቅ ተናግረዋል።
ኢሕአፓ ዛሬ ረፋድ ላይ ባወጣው አጭር መግለጫ፤ በቅርቡ ፓርቲውን በተቀላቀሉት በአቶ የሺዋስ ላይ የተወሰደውን የእስር እርምጃ ተችቷል።
የአቶ የሺዋስ እስር በሰላማዊ መንገድ የፖለቲካ እንቅስቃሴ በሚያደርጉ ዜጎች ላይ “በመንግስት እየደረሰ ያለውን አፈና” ከሚያሳዩ “ተቆጥረው የማያልቁ ድርጊቶች” ውስጥ አንዱ እንደሆነ ፓርቲው በመግለጫው ላይ አስፍሯል።
የእስር እርምጃው መጪው ምርጫ “ነጻ፣ ፍትሀዊ እና ዴሞክራሲያዊ ይሆናል” ከተባለው “በተቃራኒ እንደሚሆን አመላካች ነው” ሲል ኢህአፓ ኮንኗል።
🔴ለዝርዝሩ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2026/17394/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram