avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
11.02.2026 01:47
ሰሞኑን “ከአንዳንድ” የአማራ ክልል አካባቢዎች የመከላከያ ሰራዊትን መውጣትን ተከትሎ፤ የአማራ ክልልን ህዝብ “ለዳግም ሰብአዊ ቀውስ የሚዳርግ ሁነት ተከስቷል” ሲል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አስታወቀ።

በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ባለው ነባራዊ ሁኔታ “የተመጠነ” “የጸጥታ አካላት ስምሪት ያለመኖር” እና “የሕግ ማስከበር ስራዎች መላላት”፤ የክልሉን ህዝብ “ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈሉት ነው” ሲልም ፓርቲው ገልጿል።

አብን ይህን የገለጸው፤ የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ክልላዊ፣ ሀገራዊ እና ቀጠናዊ ወቅታዊ አጀንዳዎችን በተመለከተ ካደረገው ውይይት በኋላ ዛሬ ማክሰኞ የካቲት 3፣ 2018 ምሽት ባወጣው የአቋም መግለጫ ነው።

ፓርቲው በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ ይፋ ባደረገው በዚሁ መግለጫው፤ በአማራ ክልል “ባለፉት ጥቂት ጊዜያት” ታይቶ የነበረው “አንጻራዊ መረጋጋት” ከሰሞኑ “አይሎ” በታየ “የትጥቅ እንቅስቃሴ” መቀየሩን አትቷል።

ፓርቲው መግለጫውን ያወጣው፤ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ “የፋኖ ኃይሎች” አንዳንድ አካባቢዎችን እየተቆጣጠሩ መሆኑ እየተነገረ ባለበት ወቅት ነው።

“የፋኖ ኃይሎች” ስፍራዎቹን የተቆጣጠሩት፤ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከነበሩባቸው አካባቢዎች መንቀሳቀሳቸውን ተከትሎ እንደሆነ ከስፍራዎቹ የሚወጡ መረጃዎች አመልክተዋል።

አብን በዛሬው መግለጫው የመከላከያ ሰራዊት ከአንዳንድ አካባቢዎች “መነቃነቁን” አረጋግጧል።

ይህን ተከትሎ ከሰሞኑ “አይሎ” የታየው እንቅስቃሴ፤ የአማራን ህዝብ “ለከፋ የሰብአዊ ቀውስ፣ ለደህንነት ስጋት፣ ለኢኮኖሚ ድቀት አልፎም ለህልውና አደጋ የሚያጋልጥ” እንደሆነ አብን በመግለጫው አጽንኦት ሰጥቷል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17390/

@EthiopiaInsiderNews
14
😁 9
👎 3
👍 2
🙏 1
9 8.6K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram