የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያውያን ላይ በጣለው የጉዞ እገዳ ምክንያት ወደ አሜሪካ ከተሞች የሚጓዙ መንገደኞች ቁጥር በመቀነሱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገቢ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩን የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ተናገሩ።
አየር መንገዱ ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ 4.4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱንም ዋና ስራ አስፈጻሚው አስታውቀዋል።
አቶ መስፍን ይህን ያሉት፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የግማሽ ዓመት የስራ አፈጻጸምን በተመለከተ ዛሬ ማክሰኞ የካቲት 3፤ 2018 በአዲስ አበባው ስካይ ላይት ሆቴል በሰጡበት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።
አየር መንገዱ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 10.64 ሚሊዮን መንገደኞችን ማስተናገዱን የገለጹት ዋና ስራ አስፈጻሚው፤ በዚሁ ጊዜ ውስጥ 451 ሺህ ቶን ጭነት ማጓጓዙን አመልክተዋል።
መንግስታዊው ተቋም ባለፈው መንፈቅ ዓመት ከመንገደኞች ማጓጓዝ እና ከጭነት አገልግሎት ያገኘው አጠቃላይ ገቢ፤ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ14 በመቶ ብልጫ እንዳለው አቶ መስፍን አስታውቀዋል።
አየር መንገዱ ካገኘው አጠቃላይ ገቢ ውስጥ 22 በመቶው ከዕቃ ጭነት (ካርጎ) የተገኘ መሆኑንም ጠቁመዋል።
🔴ለዝርዝሩ➡️
https://ethiopiainsider.com/2026/17379/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram