የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ሰሜን ምስራቅ ድንበር ከዚህ ቀደም ከተቆጣጠሩት አካባቢ “የበለጠ ዘልቀው” እንደገቡ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ አስታወቁ።
በድንበር አካባቢዎች የነበሩ “የባለፉት ጥቂት ቀናት” እንቅስቃሴዎች፤ የኤርትራ መንግስት በሁለቱ ሀገራት መካከል የበረታውን ውጥረት “የበለጠ የሚያባብስ መንገድ እንደመረጠ” እንደሚጠቁሙ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
ዶ/ር ጌዲዮን ይህን የገለጹት ለኤርትራው አቻቸው ኦስማን ሳሌህ ትላንት ቅዳሜ ጥር 30፤ 2018 በጻፉት ደብዳቤ ነው።
በማህበራዊ የትስስር ገጾች የተሰራጨው ይህ ደብዳቤ፤ ትክክለኛ እንደሆነ “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምንጮች አረጋግጣለች።
ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በዚሁ ደብዳቤያቸው፤ ሁለቱ ሀገሮች በሚዋሰኑበት የኢትዮጵያ ሰሜን ምዕራብ ድንበሮች የኤርትራ ወታደሮች ከአማጺ ቡድኖች ጋር “ጥምር ወታደራዊ እንቅስቃሴ” በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል።
ይህ የኤርትራ ኃይሎች እንቅስቃሴ እና በሰሜን ምስራቅ ድንበር “የበለጠ ዘልቀው” መግባታቸው፤ “ትንኮሳዎች ብቻ ሳይሆኑ ቀጥተኛ ጥቃት ናቸው” ሲሉ ሚኒስትሩ በደብዳቤያቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።
ዶ/ር ጌዲዮን በኤርትራ መንግስት ላይ ጠንካራ ውንጀላ ያዘለ ደብዳቤ ሲጽፉ የመጀመሪያቸው አይደለም። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ባለፈው ጥቅምት ወር ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በጻፉት ደብዳቤ “አክራሪ” ያሉት የህወሓት “አንጃ” እና የኤርትራ መንግስት፤ በኢትዮጵያ ላይ “ጦርነት ለመክፈት እየተዘጋጁ ይገኛሉ” ሲሉ ከስሰው ነበር።
🔴ለዝርዝሩ➡️
https://ethiopiainsider.com/2026/17370/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram