avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
07.02.2026 15:54
ለሀገራዊ የምክክር ጉባኤ የሚቀርቡ የትግራይ ክልል አጀንዳዎች የሚሰባሰቡበትን መድረክ፤ በአዲስ አበባ ማካሄድ በአማራጭነት መያዙን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ገለጸ።

ኮሚሽኑ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተራዘመለት የስራ ዘመን ሊጠናቀቅ በመቃረቡ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄደውን የምክክር ጉባኤ “በፍጥነት” እንዲጀምር ማሳሰቢያ ተሰጥቶታል።

ማሳሰቢያውን የሰጠው፤ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑን የግማሽ ዓመት የስራ አፈጻጸም ትላንት አርብ ጥር 29፤ 2018 የገመገመው የተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራሲያዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ነው።

የኮሚሽኑን የመንፈቅ ዓመት የስራ ሪፖርት ለቋሚ ኮሚቴው ያቀረቡት፤ የተቋሙ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ናቸው።

ፕሮፌሰር መስፍን በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ አጀንዳዎችን እና ተወካዮችን የማስመረጡ ስራ ከትግራይ ክልል ውጪ ባሉ ሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳድሮች ተጠናቅቋል።

ሁሉንም ኢትዮጵያዊ በሀገራዊ ምክክር መድረክ እንዲሳተፉ ለማድረግ ኮሚሽኑ ያስቀመጠው እቅድ 93 በመቶ መሳካቱንም ዋና ኮሚሽነሩ አመልክተዋል።

የእቅድ አፈጻጸሙ በቁጥር ደረጃ ከሚጠበቀው በላይ የተከናወነ ቢሆንም፤ የትግራይ ጉዳይ ግን በቁጥር ደረጃ ብቻ ሊታይ የሚገባው አለመሆኑን ፕሮፌሰር መስፍን በትላንቱ የፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።

ይህንን ታሳቢ በማድረግም የትግራይ ክልል ወደ ሀገራዊ ምክክር መድረክ እንዲመጣ፤ ላለፉት አራት ዓመታት ብዙ ጥረቶች ሲደረጉ መቆየታቸውን አስረድተዋል።

🔴ዝርዝሩን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17359/

🔴 በቪዲዮ ለመመልከት ➡️ https://youtu.be/fEKcQTOI_Ew

@EthiopiaInsiderNews
😁 11
8
👎 4
🤮 1
3 7.6K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram