avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
07.02.2026 00:21
“ከስነ ምግባር ብልሽት” እና “ከሰብዓዊ መብት ጥሰት” ጋር በተያያዘ 104 የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላት፤ “በከባድ የዲሲፕሊን” ጥፋት መሰናበታቸውን የከተማይቱ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ጌቱ አርጋው አስታወቁ። “ብዙ እድል እና ተደጋጋሚ ትምህርት ተሰጥቷቸው” ባልታረሙ የፖሊስ አባላት ላይም “ከባድ የዲሲፒሊን እርምጃ” እንደሚወሰድ ገልጸዋል።

ኮሚሽነሩ ይህንን የገለጹት፤ ዛሬ አርብ ጥር 29፤ 2018 በተካሄደው የአዲስ አበባ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ላይ ለተነሳ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ነው። ዶ/ር ኢቲሳ ደሜ የተባሉ የከተማይቱ የምክር ቤት አባል፤ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ላይ ተደጋጋሚ ቅሬታ እንደሚነሳባቸው መስማታቸውን ገልጸዋል።

“ታች ያሉ የፖሊስ ኦፊሰሮች አካባቢ ላይ ህብረተሰቡ የሚያነሳቸው ቅሬታዎች አሉ” ያሉት ዶ/ር ኢቲሳ፤ “አንድ ሁለት ቦታ ላይ በሚፈጠረው ችግር” የፖሊስ “አጠቃላይ ስም” እንደሚጎድፍ ተናግረዋል። በህብረተሰቡ መካከል “ፖሊስ እንዲህ እየሆነ ነው። ፖሊስ እንዲህ እያደረገ ነው” የሚሉ ሰዎች መኖራቸውን የጠቀሱት የምክር ቤት አባሉ፤ ይህ አይነቱ አስተያየት የሚሰጠው “ከግንዛቤ ችግር ሊሆን እንደሚችል” ግምታቸውን አስቀምጠዋል።

“መንደር ውስጥ ገብተው የሚሰሩ የሚመሰገኑ ፖሊስ ኦፊሰሮች እንዳሉ ሁሉ፤ ቅሬታ የሚነሳባቸው መኖራቸውንም ግን በተደጋጋሚ ሰምቻለሁ” ሲሉም ዶ/ር ኢቲሳ በጸጥታ አስከባሪዎች ላይ ህብረተሰቡ የሚሰጠውን አስተያየት አጋርተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባሉ በፖሊሶች ላይ “በተለይ ከስነ ምግባር አንጻር እንዴት ነው ክትትል የሚደረገው?”፣ “ታች ድረስ ቁጥጥሩ እና ክትትሉ እስከ ምን ድረስ ነው?” ሲሉም ጠይቀዋል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17352/

@EthiopiaInsiderNews
10
👍 4
👏 4
10 7.4K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram