avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
05.02.2026 22:12
መንግስት የታሰሩ ፋኖዎች ከእስር እንዲፈቱ “በገባው ስምምነት” መሰረት ትግበራውን እየጠበቁ መሆናቸውን የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋህድ) አመራር የነበሩት መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ ገለጹ።

በአማራ ክልል የትጥቅ ትግል ሲያደርጉ ቆይተው በቅርቡ “ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል” መግባታቸውን የተናገሩት የአፋህድ አመራሮች፤ 17 አጀንዳዎችን ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ማቅረባቸውን አስታውቀዋል።

የአፋህድ አመራሮች አጀንዳዎቹን ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያስረከቡት፤ ከኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች ጋር ዛሬ ሐሙስ ጥር 28፤ 2018 በአዲስ አበባ ካካሄዱት ውይይት በኋላ ነው።

ከአመራሮቹ መካከል ባለፈው ህዳር ወር መጨረሻ አፋህድን ወክለው ከአማራ ክልል መንግስት ጋር የሰላም ስምምነት መፈራረማቸውን ያስታወቁት መቶ አለቃ ማስረሻ ይገኙበታል።

መቶ አለቃ ማስረሻ አፋህድን ወክለው የሰላም ስምምነት መፈራረማቸው ቢገለጽም፤ የድርጅቱ መሪ የሆኑት አቶ እስክንድር ነጋ ግን ግለሰቡ አስቀድመው ከድርጅቱ አመራርነታቸው መታገዳቸውን ማስታወቃቸው አይዘነጋም። አፋህድ በጉዳዩ ላይ ባወጣው መግለጫ፤ መቶ አለቃ ማስረሻን እንዳልወከላቸው መግለጹም ይታወሳል።

በዛሬው የአጀንዳ ርክክብ ስነ ስርዓት ላይ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት መቶ አለቃ ማስረሻ፤ ከአማራ ክልል መንግስት ጋር ስምምነት ከተደረሰባቸው ጉዳዮች መካከል “በእስር ላይ ያሉ የፋኖ ታጣቂዎችን መፍታት” የሚለው አንዱ እንደነበር ተናግረዋል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17302/

🔴 ቪዲዮውን ለመመልከት ➡️ https://youtu.be/VvRONPgzTGE

@EthiopiaInsiderNews
9
😁 8
👍 2
7 7K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram