avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
04.02.2026 23:26
የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ የሆኑት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፤ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው በፓርላማ ሊሾሙ ነው። የኮርፖሬሽኑ ቦርድ አባል እንዲሆኑ ከታጩት ዘጠኝ ግለሰቦች ውስጥ ስድስቱ አዳዲስ ናቸው።

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንን እንደገና ለማቋቋም በ2015 የወጣው አዋጅ፤ የተቋሙ የስራ አመራር ቦርድ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚሾሙ ይደነግጋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ ሐሙስ ጥር 28፤ 2018 በሚያካሄደው መደበኛ ስብሰባው ለኮርፖሬሽኑ ቦርድ አባልነት በዕጩነት የቀረቡለትን ግለሰቦች መርምሮ ለማጽደቅ አጀንዳ ይዟል።

የኮርፖሬሽኑ ቦርድ፤ የብሔራዊ ቴሌቪዥን እና ሬድዮ ጣቢያዎችን በስሩ የሚያስተዳድረውን ኢቢሲን በበላይነት የሚመራ አካል ነው።

ቦርዱ የመገናኛ ብዙሃንን የሚመለከቱ የመንግስት ፖሊሲዎች እና ህጎች በኮርፖሬሽኑ ተግባራዊ መሆናቸውን የማረጋገጥ ኃላፊነት በአዋጅ ተጥሎበታል።

በነገው የፓርላማ መደበኛ ሹመታቸው እንደሚጸድቅላቸው ከሚጠበቁት አዳዲስ የቦርድ አባላት መካከል ዲያቆን ዳንኤል ይገኙበታል።

ለመሰል ኃላፊነት እንግዳ ያልሆኑት ዲያቆን ዳንኤል፤ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቦርድ አባልነትን ሹመት ለሶስት ተከታታይ ጊዜያት አግኝተዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአራተኛ ጊዜ ለሹመት ፓርላማ የሚቀርቡት፤ ከእርሳቸው በፊት የኢቢሲ ቦርድን በሰብሳቢነት ይመሩ የነበሩትን ዶ/ር ለገሰ ቱሉን ለመተካት ነው።

🔴ለዝርዝሩ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17283/

@EthiopiaInsiderNews
👎 10
8
😁 3
🔥 1
12 6.1K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram