avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
04.02.2026 20:46
በፌደራል መንግስት እና በህወሓት መካከል በፕሪቶሪያ የተፈረመውን ግጭት የማቆም ስምምነት አተገባበር የሚከታተለው የባለሙያዎች ቡድን፤ ከ“እረፍት በኋላ” ዳግም ለስራ መሰማራቱን የአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ። የባለሙያዎች ቡድኑ የስምምነቱን አፈጻጸም የመከታተል “ወሳኝ ተግባራቸውን” እንደገና ጀምረዋል ብሏል።

የአፍሪካ ህብረት የፕሪቶሪያውን የግጭት ማቆም ስምምነት አፈጻጸም የመከታተል እና የማረጋገጥ ኃላፊነት የተሰጠውን ተልዕኮ ይፋ ያደረገው በታህሳስ 2015 ዓ.ም ነበር።

በዚህ ተልዕኮ ስር የተካተቱ ከኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ናይጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካ የተውጣጡ 21 ወታደራዊ እና የሲቪል ባለሙያዎች ኃላፊነታቸውን ሲወጡ ቆይተዋል።

ባለሙያዎቹ ቁጥጥር ከሚያደርጉባቸው ሂደቶች መካከል በውጊያ ሲሳተፉ የነበሩ ኃይሎች ትጥቅ መፍታት፣ እንዲበተኑ ማድረግ እና ከህብረተሰቡ ጋር መልሶ ማዋሃድን የሚመለከተው አንዱ ነው።

ከቀዬአቸው የተፈናቀሉ ሰዎች መልሶ ማስፈር፣ የኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ አገልግሎቶች ዳግም መጀመር፣ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦትን ማመቻቸት እና የሰላማዊ ሰዎችን ደህንነት ማስጠበቅን የተመለከቱ ጉዳዮችም ባለሙያዎቹ የመከታተል ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል።

እነዚህን ጉዳዮች ለመከታተል በትግራይ ክልል ተሰማርቶ የቆየው የአፍሪካውያን የባለሙያዎች ቡድን፤ “የአስተዳደር እረፍት” ወስዶ እንደነበር የአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ዛሬ ባሰራጨው መረጃ አመልክቷል።

የባለሙያዎቹ ቡድኑ ከእረፍት በኋላ በዛሬው ዕለት ወደ ስምሪት መመለሱን ቢሮው በፎቶዎች አስደግፎ አስታውቋል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17279/

@EthiopiaInsiderNews
12
😁 7
👏 3
8 5.8K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram