avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
04.02.2026 15:59
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ያለ ተቆጣጣሪ መስሪያ ቤት “ግልጽ ፈቃድ”፤ የሚንቀሳቀሱም ሆነ የማንይንቀሳቀሱ ንብረቶቻቸውን “እንዳያስተላልፉ”፣ “እንዳያስወግዱ” ወይም “እንዳይሸጡ” ተከለከሉ።

ክልከላውን የጣለው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን፤ ትዕዛዙን ተላልፈው በሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ላይ “ተገቢውን እርምጃ” እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

ባለስልጣኑ ማስጠንቀቂያውን የሰጠው፤ ትላንት ማክሰኞ ጥር 26፤ 2018 ዓ.ም. በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው “ጥብቅ ማሳሰቢያ” ነው።

በ2011 ዓ.ም. በተሻሻለው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ፤ ድርጅቶቹ ከየትኛውም ሕጋዊ ምንጭ ሀብት እና ንብረት በማሰባሰብ በህጋዊ እና ሞራላዊ ዓላማዎች ላይ ተሰማርተው መስራት እንደሚችሉ ይደነግጋል።

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በተመዘገቡበት ዓላማ መሰረት ስራቸውን ማከናወናቸውን የመቆጣጠር ኃላፊነት በአዋጅ የተሰጠው ባለስልጣኑ፤ “በህዝብ ስም የሚሰበሰቡ” ሀብትና ንብረቶችን “ለህዝብ ጥቅም መዋላቸውን” የመከታተል ኃላፊነት ተጥሎበታል።

ባለስልጣኑ ሁኔታዎችን በማጥናት እና ተጽዕኖቻቸውን በመተንተን፤ ለድርጅቶቹ ድጋፍ እና ቁጥጥርም ያደርጋል።

እነዚህን ኃላፊነቶቹን መሰረት በማድረግ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን ንብረት “የማጣራት” እና “የመመዝገብ” ስራ እያከናወነ መሆኑን መስሪያ ቤቱ ገልጿል።

ባለስልጣኑ በስም የዘረዘራቸውን የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ጥሪ ያደረገው ባለፈው ጥቅምት እና ታኅሣሥ ወራት ነበር።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17274/

@EthiopiaInsiderNews
5
👍 1
9 6K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram