በአማራ እና ትግራይ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ ከሚነሳባቸው አካባቢዎች መካከል አንዱ የሆነውን የወልቃይት ጉዳይ እርሳቸውም ሆነ የፓርላማ አባላት “እንደማይወስኑ” ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለጹ።
በወልቃይት ህዝብ ህልውና ላይ “መወሰን” የሚችለው “የእዚያው አካባቢ ህዝብ” መሆኑን ያመለከቱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የፌደራል መንግስት አቋም አሁንም ጉዳዩ “በህዝበ ውሳኔ (ሪፈረንደም) እና በህጉ አግባብ ይወሰን” የሚል መሆኑን ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ዛሬ ማክሰኞ ጥር 26፣ 2018 ከህዝብ ተወካዮች ምክር አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።
በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎችን ጉዳይ በጥያቄያቸው ያነሱት አብዱ ሀሰን የተባሉ የፓርላማ አባል፤ ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ መኖሪያቸው ለመመለስ የፌደራል መንግስት እያከናወናቸው የሚገኙ ስራዎች “በምን ደረጃ ላይ” እንደሚገኙ ጠይቀዋል።
“ህወሓት ለዓመታት ሲያደርገው እንደነበረው የተፈናቀሉ ዜጎችን ለፖለቲካ ዓላማ ሲጠቀምባቸው ይታያል” ሲሉ የወነጀሉት የፓርላማ አባሉ፤ ለተፈናቃዮች “ድጋፍ እንዳይደርስ” እና “ወደ ቀዬአቸው እንዳይመለሱ እያደረገ ይገኛል” በማለት ከስሰዋል። “ይህንን ሁኔታ ለመፍታት በፌደራል መንግስት በኩል ምን እየተሰራ ይገኛል?” ሲሉም ተያያዥ ጥያቄ አስከትለዋል።
ለጥያቄው ምላሽ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፤ በጉዳዩ ላይ የፌደራል መንግስት “ጽኑ እምነት” ያሉትን አስረድተዋል። “የወልቃይት አካባቢ ነዋሪዎች ከትግራይም ይፈናቀሉ፣ ከወልቂጤም ይፈናቀሉ፣ ከአሶሳም ይፈናቀሉ፤ ወልቃይት በሰላማዊ መንገድ መኖር 100 ፐርሰንት መብታቸው ነው” ብለዋል።
🔴ለዝርዝሩ➡️
https://ethiopiainsider.com/2026/17266/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram