avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
03.02.2026 13:22
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፤ የዛሬ ሁለት ሳምንት ገደማ በስዊትዘርላንድ ዳቮስ በተካሄደው የዓለም የኢኮኖሚ ፎረም ላይ ጎን ለጎን ከግብጹ አቻቸው ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ጋር በተወያዩበት ወቅት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የግንባታ ወጪ የሸፈነችው ሀገራቸው እንደሆነች ተናግረው ነበር።

ትራምፕ ይህን መሰል አስተያየት በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲናገሩ ቢደመጡም፤ ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳይ ላይ ይፋዊ ምላሽ ሳትሰጥ ቆይታለች።

ዛሬ ማክሰኞ ጥር 26፤ 2018 በተካሄደው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፤ የአሜሪካውን ፕሬዝዳንት በቀጥታ ባይጠቅሱም ለትራምፕ አስተያየት ምላሽ የሚመስል ንግግር አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ላይ “አንድም ብር እርዳታ”፣ “አንድም ብር ብድር አልወሰደችም” ሲሉ ለፓርላማ አባላቱ ተናግረዋል።

አብይ በጭብጨባ በታጀበው ንግግራቸው የህዳሴ ግድብ የተገነባው “በጀግኖች ኢትዮጵያዊያን ቁርጠኛ አቋም” መሆኑን አስታውቀዋል።

ግድቡ “በሀገር ውስጥም፣ በሀገር ውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን በቁርጠኝነት ጨክነው፣ በጋራ ቆመው ስለሰሩ የተከወነ ፕሮጀክት ነው” ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

@EthiopiaInsiderNews
16
👏 6
👍 4
😁 2
🥰 1
6 5.6K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram