avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
03.02.2026 12:37
የፌደራል መንግስት የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸምን በተመለከተ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዛሬ ማክሰኞ ጥር 26፤ 2018 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው የፓርላማ አባላትን ጥያቄዎችን አድምጠዋል።

ከእነዚህ የፓርላማ አባላት መካከል አንዱ የሆኑት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ተመራጭ ዶ/ር አብርሃም በርታ፤ መጪውን ምርጫ አስመልክቶ ተከታታይ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅርበዋል።

የፓርላማ አባሉ “ምርጫው ተዓማኒነቱንና ቅቡልነቱን እንዲያጣ፤ በቅድመ ምርጫ ወቅት በተለየ መልኩ የህግ ሂደቱን ባልተከተለ ሁኔታ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላቶች በዘፈቀደ እስር፣ ማዋከብ እና ማንገላታት እየተፈጸመባቸው ይገኛል። የኢዜማን አባላት ጨምሮ የታሰሩበት ሁኔታ አለ። ይህ የመወዳደሪያ ሜዳ እና ምህዳሩን በከፍተኛ ሁኔታ ያጠባል” ብለዋል።

ዶ/ር አብርሃም ያቀረቡትን ጥያቄ ይህን ሊንክ ተጭነው ያንብቡ ፦ https://www.facebook*.com/ethioelections/posts/pfbid0du2ZLX5266ZDeDXeZ78WKjcrdX7nxnirTfWHQGiW6LBAGZ34fFfnHPhsM3Zq3X24l

@EthiopiaInsiderNews
11
2 4.8K
* Принадлежит организации Meta, которая признана экстремистской и запрещена на территории РФ

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram