የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እያካሄደ ባለው መደበኛ ስብሰባው፤ የፓርላማ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጥያቄዎች አቅርበዋል።
የፌደራል መንግስትን የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም አስመልክቶ ጥያቄ ካቀረቡ አባላት መካከል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የፓርላማ ተመራጭ የሆኑት ዶ/ር አበባው ደሳለው ይገኙበታል።
ዶ/ር አበባው በጥያቄያቸው ውስጥ ካነሷቸው ጉዳዮች አንዱ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ያለው “የሰላም እጦት” ነው። ይህንኑ የተመለከተውን የፓርላማ አባሉ ጥያቄ ከዚህ በታች ቀርቧል።
“ይህንን የሰላም እጦት ለመቅረፍ በተደጋጋሚ ጊዜ የታጠቁ ኃይሎች መካከል እውነተኛ ድርድር እንዲደረግ፣ የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ፣ የንጹሃን ጥቃት እንዲቆም ላለፉት ሶስት አመታት ወትውተናል።
ሆኖም መንግስት ቀደም ብሎ ከኦሮሚያ ታጣቂዎች ጋር በቅርቡ ደግሞ በአማራ ክልል ከሚንቀሳቀሱ የታጣቂ መሪዎች ጋር ‘ድርድር አደረግኩ’ ቢልም ምንም የተሻሻለ የሰላም ሁኔታ እንደሌለ ነዋሪዎች ይገልጻሉ።
አፋብን ወይም አማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የሚል መጠሪያ ያለው 15 አመራሮችን የያዘ ድርጅት፤ አማራ ክልል ያሉ ታጣቂዎች መስርተናል እያሉ ባሉበት ወቅት መንግስት ደግሞ ‘እነዚህ ኃይሎች ከድርድር አግደናቸዋል’ ከሚሏቸው ኃይሎች ጋር ድርድር ላይ መሆኑ ለሰላሙ ምን ያህል ይጠቅማል? አዲስ ከተመሰረተው አፋብን ተብሎ ከሚጠራው ድርጅት ጋርስ መንግስት ድርድር ጀምሯል ወይ?
እውነተኛ ሰላም እንዲመጣ ከተፈለገ መንግስት አፈንግጠው ከሚወጡ ታጣቂዎች ጋር ከመደራደር፤ ለምንድን ነው ብዙ ጦር ሰራዊት ካላቸው እና በአግባቡ ከተደራጁ ታጣቂዎች ጋር እውነተኛ ድርድር አድርጎ ለሀገራችን ሰላም የማያጎናጽፈው?”
[በ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተጠናቀረ]
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram