avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
03.02.2026 01:42
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላለፉት አምስት ቀናት አቋርጧቸው የነበሩትን ወደ ትግራይ ክልል የሚደረጉ የመንገደኞች በረራዎች ከነገ ማክሰኞ ጥር 26፤ 2018 ጀምሮ ዳግም ሊጀምር እንደሆነ የተቋሙ ምንጮች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገለጹ።

አየር መንገዱ በዛሬው ዕለት የበረራ ትኬቶች ሽያጭ ሲያከናውን መዋሉን የትኬት ቢሮ ሰራተኞች እና መንገደኞች ተናግረዋል።

በመቐለ ከተማ የሚገኘው ድሪም የአውሮፕላን ትኬት መሸጫ ቢሮ፤ ለነገ ስምንት በረራዎች እንዳሉ ተገልጾላቸው ሽያጭ ሲያከናውን መዋሉን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አስታውቋል።

ለነገ በረራዎች የተዘጋጁ ሁሉም ትኬቶች ተሽጠው ማለቃቸውን የገለጸው ድርጅቱ፤ ለረቡዕ ጉዞ የሚሆኑ ትኬቶችን ከነገ ጠዋት ጀምሮ ለሽያጭ እንደሚያቀርቡ አመልክቷል።

የአየር መንገዱ በረራ ከተቋረጠባቸው የትግራይ ከተሞች መካከል አንዱ ወደ ሆነው ሽረ ከተማ፤ በነገው ዕለት ከጠዋቱ 12፡40 ጀምሮ ከአዲስ አበባ የሚነሳ በረራ እንዳለ ተቋሙ ዛሬ በድረ ገጹ ላይ ሲያስተዋውቅ ውሏል።

ከአዲስ አበባ ወደ አክሱም ከተማ ከጠዋቱ 1፡50 ጀምሮ የሚደረግ በረራ መኖሩንም የተቋሙ ድረ ገጽ በተመሳሳይ ሁኔታ አመልክቷል።

ከአክሱም ወደ አዲስ አበባ የሚደረግ የመንገደኞች በረራ በነገው ዕለት እንደሚኖር ከአየር መንገዱ መልዕክት እንደደረሳቸው ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

🔴ለዝርዝሩ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17255/

@EthiopiaInsiderNews
14
👎 1
4 5.2K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram