ከወለድ ነጻ አገልግሎት የሚሰጡ ባንኮች ከሸሪዓ መርሆዎች እና ሕግጋቶች ጋር በተጣጣመ መልኩ በመንግሥት ግምጃ ሰነድ ግብይት ላይ እንዲሳተፉ የሚያስችላቸው ስርዓት በቀጣይ ሶስት ወራት ተግባራዊ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ።
ባለፈው ስድስት ወራት ብቻ ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ የተጣራ የመንግስት የበጀት ፍላጎት በግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ ማሟላት መቻሉንም ብሔራዊ ባንክ ገልጿል።
ባንኩ ይህን የገለጸው የራሱን እና የተጠሪ ተቋማቱን የግማሽ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት፤ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፕላን በጀት እና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ ሰኞ ጥር 26፣ 2018 ባቀረበበት ወቅት ነው።
ሪፖርቱን ለቋሚ ኮሚቴው ያቀረቡት የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ፤ ተቋማቸው በቀጣዩ ሩብ ዓመት ከሚያከናውናቸው ጉዳዮች መካከል ከሸሪዓ መርሆዎች እና ሕግጋት ጋር ተስማሚነት ያለው የመንግሥት ግምጃ ቤት ሰነድ ግብይት ስርዓት ማዘጋጀት አንዱ መሆኑን አስረድተዋል።
አሁን ያለው አሰራር ከሸሪዓ መርህ ጋር አብሮ የሚሄድ ባለመሆኑ፤ ከወለድ ነጻ አገልግሎት የሚሰጡ ባንኮች በመንግሥት ግምጃ ቤት ሰነድ ላይ እንዳይሳተፉ እንዳደረጋቸው ዶ/ር እዮብ ለፓርላማ አባላቱ ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ በሸሪዓ ሕግጋት ላይ ተመሥርተው አገልግሎት የሚሰጡ ባንኮች፤ ዘምዘም፣ ሂጅራ፣ ራሚስ እና ሸበሌ ናቸው።
🔴 ለዝርዝሩ ➡️
https://ethiopiainsider.com/2026/17251/
@EthiopiaInsiderNews
Обсуждение 0
Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.
Обсудить в Telegram