avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
31.01.2026 01:59
ነዋሪዎች ከአላማጣ ከተማ እና ሌሎች አካባቢዎች እየተፈናቀሉ መሆኑን ኢሰመኮ ገለጸ

በትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተቀሰቀሰው ግጭት ለነዋሪዎች መፈናቀል ምክንያት መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ። በእነዚህ አካባቢዎች የተቀሰቀሰውን “ግጭት እና ወታደራዊ እንቅስቃሴ” ተከትሎ፤ ሁኔታው ወደ “ጦርነት” ሊሸጋገር ይችላል የሚል ሥጋት መፈጠሩን ኮሚሽኑ ገልጿል።

ብሔራዊው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ይህን የገለጸው ዛሬ አርብ ጥር 22፤ 2018 ምሽት ባወጣው መግለጫ ነው። በእነዚህ ግጭቶቹ የተቀሰቀሱት ከጥር 17፤ 2018 ጀምሮ መሆኑን ኢሰመኮ በዛሬ መግለጫው ላይ አመልክቷል።

ግጭቶቹ በወለዱት ስጋት ሳቢያ ነዋሪዎች "በኮማንድ ፖስት" ሲተዳደሩ ከቆዩት አላማጣ ከተማ እና ሌሎች አካባቢዎች “እየተፈናቀሉ” መሆናቸውን እንዲሁም በሰዎች እንቅስቃሴ ላይ “ገደቦች መጣላቸውን” እንደተገነዘበም ኮሚሽኑ ገልጿል። በተለይም “በጸለምት/ጠለምት፣ በመጋሌ እና አብአላ” አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶችን ተከትሎ፤ የሰዎችን የሕይወት፣ የአካል ደህንነት፣ ነጻነት እና ንብረት መብቶች ሥጋት ላይ የሚጥሉ ሁኔታዎች መፈጠራቸውን ኢሰመኮ ጠቅሷል።

በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም አካላት ችግሩን ከሚያባብሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ ጥሪ ያቀረበው ኢሰመኮ፤ የግጭቱ ተሳታፊዎች፤ በሲቪል ሰዎች እና መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃቶችን ከማድረስ እንዲታቀቡም አሳስቧል። እነዚህ አካላት ለግጭት መነሻ የሆኑ ልዩነቶችን “በሕግ መሠረት በምክክርና በመግባባት ለመፍታት በቁርጠኝነት እንዲሠሩ” ኮሚሽኑ ጠይቋል። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

@EthiopiaInsiderNews
11
👎 3
😱 1
6 7.1K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram