avatar
Ethiopia Insider
@EthiopiaInsiderNews
27.01.2026 22:46
የፈረንጆቹ 2026 ዓመት ከገባ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የስድስት ሀገራት ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል።

ሊገባደድ ጥቂት ቀናት በቀሩት የፈረንጆቹ ጥር ወራት፤ ዛሬ ወደ አዲስ አበባ የገቡት የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክሪስቶፈር ላንዳውን ጨምሮ ጀርመን እና ቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸውን ወደ ኢትዮጵያ ልከዋል።

የአሜሪካ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ “በቀጠናዊ የሰላም እና የጸጥታ ጉዳዮች” ላይ እንደሚወያዩ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባለፈው ሳምንት ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።

ላንዳው በዛሬው ውሏቸው፤ አብረዋቸው ወደ ኢትዮጵያ ከተጓዙት የአሜሪካ ጦር የአፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጀነራል ዳግቪን አንደርሰን ጋር በመሆን ቢሾፍቱ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ቅጽር ግቢ የተዘጋጀውን “ዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ኤክስፖ” ጎብኝተዋል።

ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ አየር ኃይልን 90ኛ ዓመት፤ ረጅም ዓመታት ላስቆጠረው የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ ግንኙነት እንደ ማሳያ ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ ራሷ እንደ ሀገር ብቻ ሳይሆን “በቀጠናው በጣም አስፈላጊ ኃይል ነች” ሲሉም ተደምጠዋል።

“እዚህ ኢትዮጵያ ያለሁት፤ ሁለቱ ሀገሮቻችን ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ ጠንካራ እና ይበልጥ የበለጸጉ እንዲሆኑ እንዴት በተሻለ ሁኔታ እንደምንተባበር እና አብረን ወደፊት እንደምንራመድ ከአመራራችሁ ጋር ለመወያየት ነው” ያሉት ላንዳው፤ “በቀጠናው ያሉትን አንዳንድ ግጭቶች ለመፍታት በጋራ ጠንካራ ሚና መጫወት እንችላለን ብለን እናስባለን” ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2026/17236/

@EthiopiaInsiderNews
14
👍 3
😁 2
9 7.8K

Обсуждение 0

Обсуждение не доступно в веб-версии. Чтобы написать комментарий, перейдите в приложение Telegram.

Обсудить в Telegram

Ethiopia Insider

17.5K
Ethiopia Insider is a digital media that provides news, updates, analysis and features.
Открыть в Telegram